የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 19:14-16

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 19:14-16 አማ2000

የፋ​ሲ​ካም የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበር፤ ጊዜ​ዉም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር፤ ጲላ​ጦ​ስም አይ​ሁ​ድን፥ “እነሆ፥ ንጉ​ሣ​ችሁ” አላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን፥ “አስ​ወ​ግ​ደው! ስቀ​ለው!” እያሉ ጮሁ። ጲላ​ጦ​ስም፥ “ንጉ​ሣ​ች​ሁን ልስ​ቀ​ለ​ውን?” አላ​ቸው፤ ሊቃነ ካህ​ና​ቱም፥ “ከቄ​ሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለ​ንም” ብለው መለሱ። ከዚህ በኋላ ሊሰ​ቅ​ሉት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ተቀ​ብ​ለው ወሰ​ዱት።