የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 15:16-20

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 15:16-20 አማ2000

እኔ መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ የመ​ረ​ጣ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ለም፤ እን​ድ​ት​ሄዱ፥ ፍሬም እን​ድ​ታ​ፈሩ፥ ፍሬ​አ​ች​ሁም እን​ዲ​ኖር፤ አብ​ንም በስሜ የም​ት​ለ​ም​ኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እን​ዲ​ሰ​ጣ​ችሁ ሾም​ኋ​ችሁ። እርስ በር​ሳ​ች​ሁም እን​ድ​ቷ​ደዱ ይህን አዝ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ። “ዓለም ቢጠ​ላ​ችሁ አስ​ቀ​ድሞ እኔን እንደ ጠላ ዕወቁ። እና​ን​ተስ ከዓ​ለም ብት​ሆኑ ዓለም በወ​ደ​ዳ​ችሁ ነበር፤ ዓለም ወገ​ኖ​ቹን ይወ​ዳ​ልና፤ ነገር ግን እኔ ከዓ​ለም መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ ከዓ​ለም አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ዓለም ይጠ​ላ​ች​ኋል። እኔ፦ ከጌ​ታው የሚ​በ​ልጥ አገ​ል​ጋይ የለም ያል​ኋ​ች​ሁን ቃሌን ዐስቡ፤ እኔን ካሳ​ደዱ እና​ን​ተ​ንም ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ቃሌን ጠብ​ቀው ቢሆ​ንስ ቃላ​ች​ሁ​ንም በጠ​በቁ ነበር።