የዮሐንስ ወንጌል 15:16-20

የዮሐንስ ወንጌል 15:16-20 አማ05

እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል። እንግዲህ እኔ የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው። “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ ዕወቁ። የዓለም ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር፤ ነገር ግን የዓለም ስላልሆናችሁና እኔ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኳችሁ፥ ዓለም ይጠላችኋል። አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን አስታውሱ፤ እኔን ካሳደዱኝ እናንተንም ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ከጠበቁ ቃላችሁንም ይጠብቃሉ።