ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 9:7-9

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 9:7-9 አማ2000

ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀ​ል​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እፈ​ት​ና​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት እን​ደ​ዚሁ አደ​ር​ጋ​ለ​ሁና። ምላ​ሳ​ቸው የተ​ሳለ ፍላጻ ነው፤ ንግ​ግ​ራ​ቸው ሽን​ገላ ነው፤ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ሰላ​ምን ይና​ገ​ራሉ፤ በል​ባ​ቸው ግን ጥላ​ቻን ይይ​ዛሉ። በውኑ ስለ​ዚህ ነገር በመ​ቅ​ሠ​ፍት አል​ጐ​በ​ኝ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?