የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 51

51
በባ​ቢ​ሎን ላይ ተጨ​ማሪ ቅጣት
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በባ​ቢ​ሎን ላይና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ የሚ​ያ​ቃ​ጥ​ልና የሚ​ያ​ጠፋ ነፋ​ስን አስ​ነ​ሣ​ለሁ። 2በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ ተሳ​ዳቢ ሰዎ​ችን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይሰ​ድ​ቧ​ታል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባዶ ያደ​ር​ጋሉ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለባ​ቢ​ሎን ወዮ​ላት” የሚል ይጨ​ም​ራል። በመ​ከ​ራም ቀን በዙ​ሪ​ያዋ ይከ​ብ​ቡ​አ​ታል። 3በቀ​ስት ወር​ዋ​ሪው ላይ፥ በጥ​ሩ​ርም በሚ​ነ​ሣው ላይ ቀስ​ተ​ኛው ቀስ​ቱን ይገ​ትር፤ ለጐ​በ​ዛ​ዝቷ አት​ዘኑ፤ ሠራ​ዊ​ቷ​ንም ሁሉ አጥፉ። 4የተ​ገ​ደ​ሉት በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር ይወ​ድ​ቃሉ፤ የቈ​ሰ​ሉ​ትም በውጭ ይወ​ድ​ቃሉ።
5“ምድ​ራ​ቸው በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ በተ​ሠ​ራው በደል የተ​ሞ​ላች ብት​ሆ​ንም፥ እስ​ራ​ኤል መበ​ለት አል​ሆ​ነ​ችም፤ ይሁ​ዳም ከአ​ም​ላኩ ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አል​ራ​ቀም። 6ከባ​ቢ​ሎን መካ​ከል ሽሹ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ፤ በበ​ደ​ልዋ አት​ጥፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እር​ሱም ብድ​ራ​ቷን ይከ​ፍ​ላ​ታ​ልና። 7ባቢ​ሎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ውስጥ ምድ​ርን ሁሉ ያሰ​ከ​ረች የወ​ርቅ ጽዋ ነበ​ረች፤ አሕ​ዛ​ብም ከጠ​ጅዋ ጠጥ​ተ​ዋል፤ ስለ​ዚህ አሕ​ዛብ ተን​ገ​ዳ​ግ​ደ​ዋል። 8ባቢ​ሎን በድ​ን​ገት ወድቃ ተሰ​ባ​ብ​ራ​ለች፤ አል​ቅ​ሱ​ላት፤ ትፈ​ወ​ስም እንደ ሆነ ለቍ​ስ​ልዋ መድ​ኀ​ኒት ውሰ​ዱ​ላት። 9ባቢ​ሎ​ንን ፈወ​ስ​ናት፥ እር​ስዋ ግን አል​ተ​ፈ​ወ​ሰ​ችም፤ ፍር​ድዋ እስከ ሰማይ ደር​ሶ​አ​ልና፥ እስከ ከዋ​ክ​ብ​ትም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ እን​ተ​ዋት፤ ሁላ​ች​ንም ወደ ሀገ​ራ​ችን እን​ሂድ። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ዳ​ች​ንን አው​ጥ​ቶ​አል፤ ኑ በጽ​ዮን የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ እን​ና​ገር።
11“ፍላ​ጾ​ችን አዘ​ጋጁ፤ ጕራ​ን​ጕ​ሬ​ዎ​ች​ንም ሙሉ፤#ዕብ. “ጋሻ​ዎ​ች​ንም አዘ​ጋጁ” ይላል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋት ዘንድ ቍጣው በባ​ቢ​ሎን ላይ ነውና የሜ​ዶ​ንን ንጉሥ መን​ፈስ አስ​ነ​ሥ​ቶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል የመ​ቅ​ደሱ በቀል#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሕ​ዝቡ በቀል” ይላል። ነውና። 12በባ​ቢ​ሎን ቅጥ​ሮች ላይ ዓላ​ማ​ውን አንሡ፤ ከጕ​ራ​ን​ጕ​ሬ​አ​ችሁ ጋር ጽኑ፤ ተመ​ል​ካ​ቾ​ችን አቁሙ፤ መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን አዘ​ጋጁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ቢ​ሎን በሚ​ኖ​ሩት ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ያደ​ርግ ዘንድ ጀም​ሮ​አ​ልና። 13አንቺ በብዙ ውኃ አጠ​ገብ የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በመ​ዝ​ገ​ብም የበ​ለ​ጠ​ግሽ ሆይ! እንደ ስስ​ትሽ መጠን ፍጻ​ሜሽ ደር​ሶ​አል። 14የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በራሱ ምሎ​አል፦ በእ​ው​ነት ሰዎ​ችን እንደ አን​በጣ እሞ​ላ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም እየ​ሮጡ ይወ​ር​ዱ​ብ​ሻል።”
15ምድ​ርን በኀ​ይሉ የፈ​ጠረ፥ ዓለ​ሙን በጥ​በቡ የመ​ሠ​ረተ፥ ሰማ​ያ​ት​ንም በማ​ስ​ተ​ዋሉ የዘ​ረጋ እርሱ ነው። 16ድም​ፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰ​ማይ ይታ​ወ​ካሉ፤ ከም​ድ​ርም ዳር ደመ​ና​ትን ያወ​ጣል፤ ለዝ​ና​ብም ጊዜ መብ​ረ​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ ነፋ​ስ​ንም ከቤተ መዛ​ግ​ብቱ ያወ​ጣል። 17ሰው ሁሉ ዕው​ቀ​ትን አጥ​ቶ​አል፥ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ሐሰ​ተ​ኞች ጣዖ​ታ​ትን ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የላ​ቸ​ው​ምና። 18ሥራ​ቸው ከንቱ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጐ​በ​ኛ​ቸው ጊዜ ይጠ​ፋሉ። 19የያ​ዕ​ቆብ ዕድል ፋንታ እንደ እነ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና። እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ነገድ ነው። ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።
20“አንቺ የጦር መሣ​ሪ​ያን በተ​ን​ሽ​ብኝ፤ እኔም ሕዝ​ቡን እበ​ት​ን​ብ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም ነገ​ሥ​ታ​ትን አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ። 21በአ​ንቺ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ሰረ​ገ​ላ​ው​ንና በላዩ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን እበ​ት​ና​ለሁ። 22በአ​ን​ቺም ወን​ድና ሴትን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤#“በአ​ን​ቺም ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን እበ​ት​ና​ለሁ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በአ​ን​ቺም ጐል​ማ​ሳ​ው​ንና ቆን​ጆ​ዪ​ቱን እበ​ት​ና​ለሁ፤ 23በአ​ን​ቺም እረ​ኛ​ው​ንና መን​ጋ​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም አራ​ሹ​ንና ጥማ​ዱን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም አለ​ቆ​ች​ንና መሳ​ፍ​ን​ትን እበ​ት​ና​ለሁ። 24በጽ​ዮን በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ በባ​ቢ​ሎ​ንና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
25“አንተ ምድ​ርን ሁሉ የም​ታ​ጠፋ አጥፊ ተራራ ሆይ! እነሆ፥ እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እጄ​ንም እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ከድ​ን​ጋ​ዮ​ቹም ላይ አን​ከ​ባ​ል​ል​ሃ​ለሁ፤ የተ​ቃ​ጠ​ለም ተራራ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ። 26ከአ​ን​ተም ለማ​ዕ​ዘን የሚ​ሆን ድን​ጋ​ይ​ንና ለመ​ሠ​ረት የሚ​ሆን ድን​ጋ​ይን አይ​ወ​ስ​ዱም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አጠ​ፋ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
27“በም​ድር ላይ ዓላ​ማን አንሡ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል መለ​ከ​ትን ንፉ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ለዩ​ባት፤ የአ​ራ​ራ​ት​ንና የሚ​ኒን#“የሚ​ኒን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የአ​ስ​ከ​ና​ዝ​ንም መን​ግ​ሥ​ታት እዘ​ዙ​ባት፤ ጦረ​ኞ​ች​ንም በላ​ይዋ አቁሙ፤ ብዛ​ታ​ቸው እንደ አን​በጣ የሆኑ ፈረ​ሶ​ችን በላ​ይዋ አውጡ። 28አሕ​ዛ​ብ​ንም፥ የሜ​ዶ​ን​ንም ነገ​ሥ​ታት፥ አለ​ቆ​ች​ንም፥ መሳ​ፍ​ን​ት​ንም ሁሉ፥ የግ​ዛ​ታ​ቸ​ው​ንም ምድር ሁሉ ለዩ​ባት። 29ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት የባ​ቢ​ሎ​ንን ምድር ባድማ ያደ​ር​ጋት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐሳብ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጸን​ቶ​አ​ልና ምድር ተና​ወ​ጠች፤ ታመ​መ​ችም። 30የባ​ቢ​ሎን ተዋ​ጊ​ዎች መዋ​ጋ​ትን ትተ​ዋል፤ በአ​ም​ባ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ጠፍ​ቶ​አል፤ እንደ ሴቶ​ችም ሆነ​ዋል፤ ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ነድ​ደ​ዋል፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተሰ​ብ​ረ​ዋል። 31ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ይነ​ግር ዘንድ ሯጩ ሯጩን ለመ​ገ​ና​ኘት፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውን ለመ​ገ​ና​ኘት ይሮ​ጣል፤ ከተ​ማዋ ከዳር እስከ ዳር ተይ​ዛ​ለ​ችና፤ 32መሻ​ገ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተይ​ዘ​ዋ​ልና፥ ቅጥ​ር​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አ​ልና፥ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ተማ​ር​ከ​ዋ​ልና።”
33የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቤት እንደ ተረ​ገጠ አው​ድማ ናት፤ ጥቂት ቈይታ የመ​ከር ጊዜ ይደ​ር​ስ​ባ​ታል። 34የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በላኝ፤ ከፋ​ፈ​ለ​ኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደ​ረ​ገኝ፤ እንደ ዘን​ዶም ዋጠኝ፤ ከሚ​ጣ​ፍ​ጠ​ውም#ዕብ. “እኔ​ንም ጣለኝ” የሚል ይጨ​ም​ራል። ሥጋዬ ሆዱን ሞላ። 35በጽ​ዮን የም​ት​ኖር በእኔ ላይ የተ​ደ​ረገ ግፍና ሥቃይ በባ​ቢ​ሎን ላይ ይሁን ትላ​ለች፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደሜ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ ይሁን ትላ​ለች።” 36ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የሚ​ገ​ፋ​ሽን እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ በቀ​ል​ሽ​ንም እበ​ቀ​ል​ል​ሻ​ለሁ፤ ባሕ​ር​ዋ​ንም ድርቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ምን​ጭ​ዋ​ንም አደ​ር​ቃ​ለሁ። 37ባቢ​ሎ​ንም ባድ​ማና የቀ​በሮ ማደ​ሪያ፥ ማፍ​ዋ​ጫም ትሆ​ና​ለች፤#“የቀ​በሮ ማደ​ሪያ፥ ማፍ​ዋ​ጫም ትሆ​ና​ለች” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ሰው አይ​ገ​ኝም። 38በአ​ን​ድ​ነ​ትም እንደ አን​በ​ሶች ያገ​ሣሉ፤ እንደ አን​በ​ሳም ደቦ​ሎች ያጕ​ረ​መ​ር​ማሉ። 39በሞ​ቃ​ቸው ጊዜ እን​ዲ​ዝሉ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም እን​ቅ​ልፍ እን​ዲ​ተኙ መጠ​ጥን አጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አሰ​ክ​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ ከዚ​ያም በኋላ አይ​ነ​ቁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 40እንደ ጠቦ​ቶ​ችና እንደ አውራ በጎች፥ እንደ አውራ ፍየ​ሎ​ችም ወደ መታ​ረድ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።
41“የም​ድ​ርም ሁሉ ክብር#ዕብ. “ሼሻክ” ይላል። እን​ዴት ተያ​ዘች! እን​ዴ​ትስ ተወ​ሰ​ደች! ባቢ​ሎን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዴት ለጥ​ፋት ሆነች! 42ባሕር በባ​ቢ​ሎን ላይ ወጣ፤ በሞ​ገ​ዱም ብዛት ተከ​ደ​ነች። 43ከተ​ሞ​ችዋ ባድ​ማና ደረቅ ምድር፥ ሰውም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት፥ የሰ​ውም ልጅ የማ​ያ​ል​ፍ​በት ምድር ሆኑ። 44በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤#ዕብ “በባ​ቢ​ሎን ውስጥ ቤልን እቀ​ጣ​ለሁ” ይላል። የዋ​ጠ​ች​ው​ንም ከአ​ፍዋ አስ​ተ​ፋ​ታ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብም ከዚያ ወዲያ ወደ እር​ስዋ አይ​ሰ​በ​ሰ​ቡም፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ቅጥ​ሮች ይወ​ድ​ቃሉ።
45“ሕዝቤ ሆይ! ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ ራሳ​ች​ሁን አድኑ። 46በም​ድ​ርም ከሚ​ሰማ ወሬ የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ ልባ​ች​ሁም የዛለ አይ​ሁን፤ በአ​ንድ ዓመት ወሬ ይመ​ጣል፤ ከዚ​ያም በኋላ በሌ​ላው ዓመት ወሬ ይመ​ጣል፤ በም​ድ​ርም ላይ ግፍ ይነ​ግ​ሣል፤ አለ​ቃም በአ​ለቃ ላይ ይነ​ሣል። 47ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን የባ​ቢ​ሎ​ንን ምስ​ሎች የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፤ ምድ​ር​ዋም ሁሉ ትደ​ር​ቃ​ለች፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም የሞ​ቱት ሁሉ በመ​ካ​ከ​ልዋ ይወ​ድ​ቃሉ። 48አጥ​ፊ​ዎች ከሰ​ሜን ይመ​ጡ​ባ​ታ​ልና ሰማ​ይና ምድር፥ በእ​ነ​ር​ሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢ​ሎን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።#ምዕ. 51 ከቁ. 45 እስከ 48 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 49ባቢ​ሎ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተገ​ደ​ሉት ትወ​ድ​ቃ​ለች፤ ስለ ባቢ​ሎ​ንም በም​ድር ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።
50“ከሰ​ይፍ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ ሆይ! ሂዱ፤ አት​ቁሙ፤ በሩቅ ያላ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስቡ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በል​ባ​ችሁ አስቡ። 51ስድ​ባ​ች​ንን ስለ ሰማን አፍ​ረ​ናል፤ ባዕ​ዳን ሰዎ​ችም ወደ ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገብ​ተ​ዋ​ልና ውር​ደት ፊታ​ች​ንን ከድ​ኖ​ታል። 52ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ች​ዋን የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ር​ዋም ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ። 53ባቢ​ሎ​ንም ወደ ሰማይ ብት​ወጣ፥ ቅፅ​ሮ​ች​ዋ​ንም በኀ​ይ​ልዋ ብታ​ጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥ​ፊ​ዎች ይመ​ጡ​ባ​ታል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
54“ከባ​ቢ​ሎን የጩ​ኸት ድምፅ፥ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር የታ​ላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰ​ም​ቶ​አል። 55እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባቢ​ሎ​ንን አጥ​ፍ​ቶ​አ​ታ​ልና፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ሞገዱ እንደ ብዙ ውኃ​ዎች የሚ​ተ​መ​ውን ታላ​ቁን ድምፅ ዝም አሰ​ኝ​ቶ​አ​ልና፤ የድ​ም​ፃ​ቸው ጩኸት ተሰ​ም​ቶ​አል። 56ጥፋት#ዕብ. “አጥ​ፊው” ይላል። በባ​ቢ​ሎን ላይ መጥ​ቶ​ባ​ታ​ልና፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ችዋ ተያዙ፤ ቀስ​ታ​ቸ​ውም ተሰ​ባ​በረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተበ​ቅ​ሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍዳን ከፍ​ሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና። 57መሳ​ፍ​ን​ቶ​ች​ዋ​ንና ጥበ​በ​ኞ​ች​ዋ​ንም፥ አለ​ቆ​ች​ዋ​ንና ሹሞ​ች​ዋን፥ ኀያ​ላ​ኖ​ች​ዋ​ንም አሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አን​ቀ​ላ​ፍ​ተው አይ​ነ​ቁም#“ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አን​ቀ​ላ​ፍ​ተው አይ​ነ​ቁም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ይላል ስሙ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ለው ንጉሥ። 58የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሰፊው የባ​ቢ​ሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈ​ር​ሳል፤ ረጃ​ጅ​ሞች በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሕዝቡ ለከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ አሕ​ዛ​ብም በመ​ጀ​መ​ሪያ በእ​ሳት ያል​ቃሉ።”
ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ወደ ባቢ​ሎን መል​እ​ክት እንደ ላከ
59የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት ከእ​ርሱ ዘንድ ወደ ባቢ​ሎን በሄደ ጊዜ ለማ​ሴው ልጅ ለኔ​ርዩ ልጅ ለሠ​ራያ ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ያዘ​ዘው ቃል ይህ ነው። 60ሠራ​ያም የቤቱ አዛዥ ነበረ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ የሚ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢ​ሎን የተ​ጻ​ፈ​ውን ይህን ቃል ሁሉ ኤር​ም​ያስ በአ​ንድ መጽ​ሐፍ ላይ ጻፈው። 61ኤር​ም​ያ​ስም ሠራ​ያን እን​ዲህ አለው፥ “ወደ ባቢ​ሎን በገ​ባህ ጊዜ እይ፤ ይህ​ንም ቃል ሁሉ አን​ብ​ብና፦ 62አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ እን​ድ​ት​ሆን ታጠ​ፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተና​ግ​ረ​ሃል በል። 63ይህ​ንም መጽ​ሐፍ ማን​በብ ከፈ​ጸ​ምህ በኋላ፥ ድን​ጋ​ይን እሰ​ር​በት፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥ​ስም ወንዝ ውስጥ ጣለው። 64አን​ተም፦ እኔ ከማ​መ​ጣ​ባት ክፉ ነገር የተ​ነሣ እን​ዲሁ ባቢ​ሎን ትሰ​ጥ​ማ​ለች፤ አት​ነ​ሣ​ምም በል።”
የኤ​ር​ም​ያስ ቃል እስ​ከ​ዚህ ድረስ ነው።#ምዕ. 51 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 28 ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ