ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 43

43
ኤር​ም​ያስ ወደ ግብፅ እንደ ተወ​ሰደ
1የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሁሉ፥ ለእ​ነ​ርሱ አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከ​ውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤር​ም​ያስ ለሕ​ዝቡ ሁሉ መና​ገ​ርን በፈ​ጸመ ጊዜ እን​ዲህ ሆነ፤ 2የኢ​ዮ​ስ​ያስ#ዕብ. “ሆሻያ” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “ማሲያ” ይላል። ልጅ ኣዛ​ር​ያስ፥ የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችም ሰዎች ሁሉ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “ሐሰት ተና​ግ​ረ​ሃል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚያ ትቀ​መጡ ዘንድ ወደ ግብፅ አት​ግቡ ብሎ አል​ላ​ከ​ህም፤ 3ነገር ግን ከለ​ዳ​ው​ያን እን​ዲ​ገ​ድ​ሉን ወደ ባቢ​ሎ​ንም እን​ዲ​ያ​ፈ​ል​ሱን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠን ዘንድ የኔ​ርዩ ልጅ ባሮክ በላ​ያ​ችን ላይ አነ​ሣ​ሥ​ቶ​ሃል” አሉት።
4የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ በይ​ሁዳ ምድር ይቀ​መጡ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ሙም። 5የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ በይ​ሁዳ ምድር ለመ​ቀ​መጥ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​ባ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ለ​ሱ​ትን የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ። 6ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንም፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሴቶች ልጆች፥ የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከሳ​ፋን ልጅ ከአ​ኪ​ቃም ልጅ ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር የተ​ዋ​ቸ​ውን ሰዎች ሁሉ፥ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስ​ንና የኔ​ር​ዩን ልጅ ባሮ​ክ​ንም ወሰዱ። 7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አል​ሰ​ሙ​ምና ወደ ግብፅ ምድር ገቡ፤ እስከ ጣፍ​ናስ ድረ​ስም መጡ።
8በጣ​ፍ​ና​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 9“ታላ​ላ​ቆ​ችን ድን​ጋ​ዮች በእ​ጅህ ውሰድ፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች እያዩ በጣ​ፍ​ናስ ባለው በፈ​ር​ዖን ቤት ደጅ መግ​ቢያ ሸሽ​ጋ​ቸው። 10እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪ​ያ​ዬን የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፤ ዙፋ​ኑ​ንም እኔ በሸ​ሸ​ግ​ኋ​ቸው በእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤ ጋሻ​ዎ​ቹ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ ያነ​ሣል።#ዕብ. “እር​ሱም ማለ​ፊ​ያ​ውን ድን​ኳ​ኑን በላ​ያ​ቸው ይዘ​ረ​ጋል” ይላል። 11መጥ​ቶም የግ​ብ​ፅን ምድር ይመ​ታል፤ ለሞ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሞት፥ ለም​ር​ኮም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለም​ርኮ፥ ለሰ​ይ​ፍም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል። 12በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ቤቶች እሳ​ትን ያነ​ድ​ዳል፤ ያቃ​ጥ​ላ​ቸ​ው​ማል፤ ይማ​ር​ካ​ቸ​ው​ማል፤ እረ​ኛም ልብ​ሱን እን​ደ​ሚ​ቀ​ምል እን​ዲሁ የግ​ብ​ፅን ሀገር ይቀ​ም​ላ​ታል፤#ዕብ. “እረኛ ደበ​ሎ​ውን እን​ደ​ሚ​ደ​ርብ እን​ዲሁ የግ​ብ​ፅን አገር ይደ​ር​ባል” ይላል። ከዚ​ያም በሰ​ላም ይወ​ጣል። 13በግ​ብፅ ምድ​ርም ያለ​ውን የፀ​ሐይ ከተማ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኦን” ይላል። ምሰ​ሶ​ዎ​ችን ይሰ​ብ​ራል፥ የግ​ብ​ፅ​ንም አማ​ል​ክት ቤቶች በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላል።”#ምዕ. 43 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 50 ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ