ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 40

40
ኤር​ም​ያስ ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር እንደ ተቀ​መጠ
1ወደ ባቢ​ሎን በተ​ማ​ረ​ኩት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች መካ​ከል የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን በሰ​ን​ሰ​ለት አስሮ በወ​ሰ​ደው ጊዜ ከራማ ከለ​ቀ​ቀው በኋላ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። 2የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ኤር​ም​ያ​ስን ወሰ​ደው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተና​ገረ። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አደ​ረገ፤ እር​ሱን በድ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ይህ ነገር ሆነ​ባ​ችሁ። 4አሁ​ንም እነሆ በእ​ጅህ ካለ​ችው ሰን​ሰ​ለት ዛሬ ፈታ​ሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ቢታ​ይህ፥ ና፤ እኔም በመ​ል​ካም አይ​ሃ​ለሁ፤#ቀጣዩ የ4 ቍጥር ክፍል በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ባይ​ታ​ይህ ግን፥ ተቀ​መጥ፤ ተመ​ል​ከት፥ እነሆ፥ ሀገ​ሪቱ ሁሉ በፊ​ትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መል​ካም መስሎ በሚ​ታ​ይ​ህና ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህም ስፍራ ተቀ​መጥ።” 5እር​ሱም ገና ሳይ​መ​ለስ፥ “የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪ​ቃም ልጅ ወደ ጎዶ​ል​ያስ ተመ​ለስ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በሕ​ዝቡ መካ​ከል በይ​ሁዳ ምድር ተቀ​መጥ፤ ወይም ትሄድ ዘንድ ለዐ​ይ​ንህ ደስ ወደ​ሚ​ያ​ሰ​ኝህ ስፍራ ሂድ” አለው። የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ስን​ቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰ​ና​በ​ተው። 6ኤር​ም​ያ​ስም የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ወደ አለ​በት ወደ መሴፋ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በሀ​ገሩ ውስጥ በቀ​ሩት ሕዝብ መካ​ከል ተቀ​መጠ።
ጎዶ​ል​ያስ የይ​ሁዳ ገዥ ሆኖ መሾሙ
7በየ​ሜ​ዳው የነ​በ​ሩት የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችና ሰዎ​ቻ​ቸው ሁሉ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በሀ​ገሩ ላይ እንደ ሾመ፥ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን ልጆ​ች​ንም፥ ወደ ባቢ​ሎን ያል​ተ​ማ​ረ​ኩ​ት​ንም የም​ድ​ርን ድሆች እን​ዳ​ስ​ጠ​በቀ በሰሙ ጊዜ፥ 8የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል፥ የቃ​ር​ሔም ልጆች ዮሐ​ና​ንና#ግእዝ “በዓ​ሊም” ይላል። ዮና​ታን፥ የተ​ን​ሁ​ሜ​ትም ልጅ ሠራያ፥ የነ​ጦ​ፋ​ዊ​ውም የዮፌ ልጆች፥ የመ​ከጢ ልጅ አዛ​ን​ያም ከሰ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር ወደ ጎዶ​ል​ያስ ወደ መሴፋ መጡ። 9የሳ​ፋ​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ለእ​ነ​ር​ሱና ለሰ​ዎ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ብሎ ማለ፥ “ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን ትገዙ ዘንድ አት​ፍሩ፤ በም​ድር ተቀ​መጡ፤ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ተገዙ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል። 10እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚ​መ​ጡት ከለ​ዳ​ው​ያን ፊት እቆም ዘንድ በመ​ሴፋ እኖ​ራ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ወይ​ኑ​ንና ፍሬ​ውን፥ ዘይ​ቱ​ንም አከ​ማቹ፤ በየ​ዕ​ቃ​ች​ሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያ​ዛ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​መጡ።”
11በሞ​ዓ​ብና በአ​ሞ​ንም ልጆች መካ​ከል፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ የነ​በሩ አይ​ሁድ ሁሉ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ እን​ዳ​ስ​ቀረ፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በላ​ያ​ቸው እንደ ሾመው ሰሙ። 12አይ​ሁ​ድም ሁሉ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​በት ስፍራ ሁሉ ተመ​ለሱ፤ ወደ ይሁ​ዳም ሀገር ጎዶ​ል​ያስ ወዳ​ለ​በት ወደ መሴፋ መጡ፤ ወይ​ን​ንና የበ​ጋን ፍሬ፥ ዘይ​ት​ንም እጅግ ብዙ አከ​ማቹ።
የጎ​ዶ​ል​ያስ መገ​ደል
13የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ በየ​ሜ​ዳ​ውም የነ​በሩ የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ ወደ ጎዶ​ል​ያስ ወደ መሴፋ መጥ​ተው፦ 14“የአ​ሞን ልጆች ንጉሥ በኣ​ሊስ ይገ​ድ​ልህ ዘንድ የና​ታ​ን​ያን ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን እንደ ላከ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አሉት። የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ግን አላ​መ​ና​ቸ​ውም። 15የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ “እባ​ክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያ​ውቅ የና​ታ​ን​ያን ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን ልግ​ደ​ለው፤ ወደ አንተ የተ​ሰ​በ​ሰቡ አይ​ሁድ ሁሉ እን​ዲ​በ​ተኑ፥ የይ​ሁ​ዳም ቅሬታ እን​ዲ​ጠፋ ነፍ​ስ​ህን ስለ ምን ይገ​ድ​ላል?” ብሎ በመ​ሴፋ በቈ​ይታ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ተና​ገረ። 16የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ግን የቃ​ር​ሔን ልጅ ዮሐ​ና​ንን፥ “በእ​ስ​ማ​ኤል ላይ ሐሰት ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ” አለው።#ምዕ. 40 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 47 ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ