ትንቢተ ኤርምያስ 37
37
ሴዴቅያስ ለኤርምያስ ያቀረበው ጥያቄ
1የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ። 2እርሱም ሆነ፥ አገልጋዮቹ፥ የሀገሩም ሕዝብ በነቢዩ በኤርምያስ እጅ የተናገረውን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
3ንጉሡም ሴዴቅያስ፥ “ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የማሴውን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ። 4እርሱንም በግዞት ቤት ገና አላገቡትም ነበርና ኤርምያስ በሕዝቡ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በከተማው” ይላል። መካከል ይወጣና ይገባ ነበር። 5የፈርዖንም ሠራዊት ከግብፅ ወጣ፤ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬአቸውን በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ።
6የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ 7የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ከእኔ ትጠይቁ ዘንድ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ እነሆ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ ሀገሩ ወደ ግብፅ ይመለሳል። 8ከለዳውያንም ተመልሰው ይህችን ከተማ ይዋጉአታል፤ ይይዙአትማል፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል። 9እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አይሄዱምና፦ ከለዳውያን በርግጥ ከእኛ ዘንድ ይሄዳሉ ብላችሁ ራሳችሁን አታታልሉ። 10ነገር ግን እናንተን የሚወጉትን የከለዳውያንን ጭፍራ ሁሉ ብትመቱ፤ ከእነርሱም ጥቂት ተወግተው ያልሞቱ ቢቀሩ ሁሉ እያንዳንዱ በስፍራው ይነሣሉ፤ ይህቺንም ሀገር በእሳት ያቃጥላሉ።”
11የከለዳውያንም ሠራዊት ከፈርዖን ሠራዊት ፊት የተነሣ ከኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ እንዲህ ሆነ፤ 12ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ይኖር ዘንድ ወደ ብንያም ሀገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ። 13በብንያምም በር በነበረ ጊዜ የሐናንያ ልጅ የሰሌምያ ልጅ ሳሩያ#ዕብ. “የሪያ” ይላል። የተባለ በር ጠባቂ በዚያ ነበረ፤ እርሱም፥ “ወደ ከለዳውያን መኰብለልህ ነው” ብሎ ነቢዩን ኤርምያስን ያዘው። 14ኤርምያስም፥ “ሐሰት ነው፤ ወደ ከለዳውያን መኰብለሌ አይደለም” አለ፤ እርሱ ግን አልሰማውም፤ ሳሩያም ኤርምያስን ይዞ ወደ አለቆች አመጣው። 15አለቆችም በኤርምያስ ላይ ተቈጥተው መቱት፤ የግዞት ቤት አድርገውት ነበርና ወደ ጸሓፊው ወደ ዮናታን ቤት ላኩት።
16ኤርምያስም ወደ ጕድጓድ ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፤ ኤርምያስም በዚያ ብዙ ቀን ተቀመጠ። 17ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፥ “በውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በቈይታ ጠየቀው። ኤርምያስም፥ “አዎን አለ፤ ደግሞም በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ” አለው። 18ኤርምያስም ደግሞ ንጉሡን ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፥ “በግዞት ቤት የጣላችሁኝ አንተን፥ ወይስ አገልጋዮችህን፥ ወይስ ሕዝብህን ምን በድያችሁ ነው? 19የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች ሀገር አይመጣባችሁም ብለው ትንቢት ይናገሩላችሁ የነበሩ ነቢያቶቻችሁ ወዴት አሉ? 20አሁንም አቤቱ ንጉሥ ሆይ! ልመናዬ ወደ አንተ ይድረስ፤ በዚያ እንዳልሞት ወደ ጸሓፊው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ።” 21ንጉሡም ሴዴቅያስ አዘዘ፤ ኤርምያስንም በግዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖሩት፤ እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከውጪ ጋጋሪዎች እያመጡ ይሰጡት ነበር። እንዲሁም ኤርምያስ በግዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀምጦ ነበር።#ምዕ. 37 በግሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 44 ነው።
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 37: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ