ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 33:23-26

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 33:23-26 አማ2000

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ “ይህ ሕዝብ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ወገን ጥሎ​አ​ቸ​ዋል፥ እን​ዲሁ በፊ​ታ​ቸው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሕዝብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝ​ቤን አቃ​ል​ለ​ዋል ያለ​ውን ነገር አት​መ​ለ​ከ​ት​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የቀ​ንና የሌ​ሊት ቃል ኪዳ​ኔን የሰ​ማ​ይ​ንና የም​ድ​ር​ንም ሥር​ዐት ያላ​ጸ​ናሁ እንደ ሆነ፥ እኔም ደግሞ በአ​ብ​ር​ሃ​ምና በይ​ስ​ሐቅ በያ​ዕ​ቆ​ብም ዘር ላይ ገዢ​ዎች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እን​ዳ​ላ​ስ​ነሣ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንና የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘር እጥ​ላ​ለሁ፤ ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥ እም​ራ​ቸ​ው​ማ​ለ​ሁና።”