የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 3:1-11

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 3:1-11 አማ2000

የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ጦር​ነት ሁሉ ያላ​ወ​ቁ​ትን እስ​ራ​ኤ​ልን በእ​ነ​ርሱ ይፈ​ት​ና​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ተዋ​ቸው። ይህም ጦር​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ትው​ልድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ በፊት የነ​በ​ሩት እነ​ዚ​ህን አላ​ወ​ቋ​ቸ​ውም ነበር፤ እነ​ር​ሱም አም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መኳ​ን​ንት፥ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከበ​ዓ​ል​ሄ​ር​ሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ በሊ​ባ​ኖስ ተራራ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ያዘ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ መስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲ​ታ​ወቅ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ተ​ኑ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ዚህ ቀሩ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ በኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም መካ​ከል ተቀ​መጡ። ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም አገ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው ሰጡ፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አመ​ለኩ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተው በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ። ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በወ​ን​ዞ​ችም መካ​ከል ባለች በሶ​ርያ ንጉሥ በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ስም​ንት ዓመት ተገ​ዙ​ለት። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል መድ​ኀ​ኒ​ትን አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው። የካ​ሌብ የታ​ናሽ ወን​ድሙ የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያ​ልም አዳ​ና​ቸው፤ ለእ​ር​ሱም ታዘ​ዙ​ለት። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ ለጦ​ር​ነ​ትም ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በወ​ን​ዞች መካ​ከል ያለች የሶ​ርያ ንጉሥ ኩሳ​ር​ሳ​ቴ​ምን በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ላይ በረ​ታች። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ዐረ​ፈች፤ የቄ​ኔ​ዝም ልጅ ጎቶ​ን​ያል ሞተ።