የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 3

3
ሳይ​ባ​ረሩ በም​ድ​ሪቱ ስለ ቀሩት ሕዝብ
1የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ጦር​ነት ሁሉ ያላ​ወ​ቁ​ትን እስ​ራ​ኤ​ልን በእ​ነ​ርሱ ይፈ​ት​ና​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ተዋ​ቸው። 2ይህም ጦር​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ትው​ልድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ በፊት የነ​በ​ሩት እነ​ዚ​ህን አላ​ወ​ቋ​ቸ​ውም ነበር፤ 3እነ​ር​ሱም አም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መኳ​ን​ንት፥ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከበ​ዓ​ል​ሄ​ር​ሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ በሊ​ባ​ኖስ ተራራ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፤ 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ያዘ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ መስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲ​ታ​ወቅ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ተ​ኑ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ዚህ ቀሩ። 5የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ በኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም መካ​ከል ተቀ​መጡ። 6ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም አገ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው ሰጡ፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አመ​ለኩ።
ጎቶ​ን​ያል
7የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተው በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ። 8ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በወ​ን​ዞ​ችም መካ​ከል ባለች በሶ​ርያ ንጉሥ በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ስም​ንት ዓመት ተገ​ዙ​ለት። 9የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል መድ​ኀ​ኒ​ትን አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው። የካ​ሌብ የታ​ናሽ ወን​ድሙ የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያ​ልም አዳ​ና​ቸው፤ ለእ​ር​ሱም ታዘ​ዙ​ለት። 10የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ ለጦ​ር​ነ​ትም ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በወ​ን​ዞች መካ​ከል ያለች የሶ​ርያ ንጉሥ ኩሳ​ር​ሳ​ቴ​ምን በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ላይ በረ​ታች። 11ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ዐረ​ፈች፤ የቄ​ኔ​ዝም ልጅ ጎቶ​ን​ያል ሞተ።
ናዖድ
12የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሞ​ዓ​ብን ንጉሥ ዔግ​ሎ​ምን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አበ​ረ​ታ​ባ​ቸው። 13የአ​ሞ​ንን ልጆ​ችና አማ​ሌ​ቅን ወደ እርሱ ሰበ​ሰበ፤ ሄዶም እስ​ራ​ኤ​ልን መታ፤ ዘን​ባባ ያለ​ባ​ት​ንም ከተማ ያዘ። 14የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለሞ​ዓብ ንጉሥ ለዔ​ግ​ሎም ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ተገዙ።
15የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብን​ያ​ማ​ዊ​ውን የጌ​ራን ልጅ ናዖ​ድን#ዕብ. “ኤሁድ” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “አወድ” ይለ​ዋል። ሁለቱ እጆቹ ቀኝ የሆ​ኑ​ለ​ትን ሰው አዳኝ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግ​ሎም እጅ መንሻ ላኩ። 16ናዖ​ድም ሁለት አፍ ያላት ርዝ​መቷ አንድ ስን​ዝር የሆ​ነች ሰይፍ አበጀ፤ ከል​ብ​ሱም በታች በቀኝ በኩል በወ​ገቡ ታጠ​ቃት። 17ለሞ​ዓ​ብም ንጉሥ ለዔ​ግ​ሎም እጅ መን​ሻ​ውን አቀ​ረበ፤ ዔግ​ሎ​ምም እጅግ ወፍ​ራም ሰው ነበረ። 18እጅ መን​ሻ​ው​ንም ማቅ​ረብ በጨ​ረሰ ጊዜ፥ እጅ መንሻ የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሰዎች አሰ​ና​በ​ታ​ቸው። 19ዔግ​ሎ​ምም ከገ​ል​ገል ከጣ​ዖ​ታቱ ቤት ተመ​ለሰ። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብ​ቻህ የም​ነ​ግ​ርህ የም​ሥ​ጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግ​ሎ​ምም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ወጣ አዘዘ፤ በእ​ር​ሱም ዘንድ የቆ​ሙት ሁሉ ወጡ ። 20ናዖ​ድም ወደ እርሱ ገባ፤ እር​ሱም በበጋ ቤቱ ሰገ​ነት ለብ​ቻው ተቀ​ምጦ ነበር። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክት ለአ​ንተ አለኝ” አለው። ዔግ​ሎ​ምም ከዙ​ፋኑ ተነሣ፥ ቀረ​በ​ውም። 21ናዖ​ድም በተ​ነሣ ጊዜ ግራ እጁን ዘር​ግቶ ከቀኝ ጎኑ ሰይ​ፉን መዘዘ፤ ዔግ​ሎ​ም​ንም ሆዱን ወጋው፤ 22እስከ ውላ​ጋ​ዋም አስ​ገ​ባት፤ እስከ ጀር​ባ​ውም በረ​በ​ረው፥ ሰይ​ፉ​ንም ከሆዱ መልሶ አላ​ወ​ጣ​ትም። 23ናዖ​ድም የእ​ል​ፍ​ኙን ደጅ ዘግ​ቶና ቈልፎ ወደ ውጭ ወጣ።
24ናዖ​ድም ከሄደ በኋላ አገ​ል​ጋ​ዮቹ መጡ፤ የሰ​ገ​ነ​ቱም ደጅ ተቈ​ልፎ ባዩ ጊዜ፥ “ምና​ል​ባት በበጋ ሰገ​ነቱ ውስጥ ወገ​ቡን ይሞ​ክር ይሆ​ናል” አሉ። 25እስ​ኪ​ያ​ፍ​ሩም ድረስ ቈዩ፤ የሰ​ገ​ነ​ቱ​ንም ደጅ እን​ዳ​ል​ከ​ፈተ ባዩ ጊዜ መክ​ፈ​ቻ​ውን ወስ​ደው ከፈቱ፤ እነ​ሆም፥ ጌታ​ቸው በም​ድር ላይ ወድቆ ሞቶም አገ​ኙት።
26እስ​ከ​ሚ​ታ​ወ​ኩም ድረስ ናዖድ አመ​ለጠ፤ ያወ​ቀ​ውም የለም፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አልፎ ወደ ሴይ​ሮታ አመ​ለጠ። 27ከዚ​ህም በኋላ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር በደ​ረሰ ጊዜ በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ራም ሀገር ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከእ​ርሱ ጋር ከተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ወረዱ፤ እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው ሄደ። 28እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ና​ልና ተከ​ተ​ሉኝ” አላ​ቸው። ተከ​ት​ለ​ው​ትም ወረዱ፤ ወደ ሞዓ​ብም የሚ​ያ​ሻ​ግ​ረ​ውን የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን መሻ​ገ​ርያ ያዙ፤ ማንም ሰው እን​ዲ​ያ​ልፍ አል​ፈ​ቀ​ዱም። 29በዚ​ያም ወራት ከሞ​ዓብ ዐሥር ሺህ የሚ​ያ​ህ​ሉ​ትን፥ ጐል​ማ​ሶ​ችና ጽኑ​ዓን ሁሉ ገደሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው እንኳ አላ​መ​ለ​ጠም። 30በዚ​ያም ወራት ሞዓ​ባ​ው​ያን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ ገቡ፤ ምድ​ሪ​ቱም ሰማ​ንያ ዓመት ዐረ​ፈች። ናዖ​ድም እስ​ኪ​ሞት ድረስ ገዛ​ቸው።
ሴሜ​ጋር
31ከእ​ር​ሱም በኋላ የሐ​ናት ልጅ ሴሜ​ጋር ተነሣ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ስድ​ስት መቶ ሰው በበሬ መው​ጊያ ገደለ፤ እር​ሱም ደግሞ እስ​ራ​ኤ​ልን አዳነ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ