የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 2

2
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በቀ​ላ​ው​ት​ም​ኖስ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከገ​ል​ገላ ወደ ቀላ​ው​ት​ም​ኖስ ወደ ቤቴል ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ወጥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቼ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ እሰ​ጣ​ች​ሁም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር አግ​ብ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም፦ ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አላ​ፈ​ር​ስም፤ 2እና​ን​ተም በዚች ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርጉ፤ ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸው፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ስበሩ፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ው​ንም አፍ​ርሱ አልሁ። እና​ንተ ግን ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ ይህ​ንስ ለምን አደ​ረ​ጋ​ችሁ? 3ስለ​ዚ​ህም እኔ አሕ​ዛ​ብን ከፊ​ታ​ችሁ አላ​ወ​ጣ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ያስ​ጨ​ን​ቋ​ች​ኋል፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወጥ​መድ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል” አልሁ። 4የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ይህን ቃል ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በተ​ና​ገረ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ሥ​ተው አለ​ቀሱ። 5የዚ​ያም ስፍራ ስም “መካነ ብካይ” ተብሎ ተጠራ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠዉ።
የኢ​ያሱ ሞት
6ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን ባሰ​ና​በተ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ምድ​ሪ​ቱን ሊወ​ርሱ ወደ​የ​ር​ስ​ታ​ቸው ገቡ። 7ኢያ​ሱም በነ​በ​ረ​በት ዘመን ሁሉ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን ታላ​ቁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ ባወ​ቁት፥ ከኢ​ያሱ በኋላ በነ​በሩ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዘመን ሁሉ ሕዝቡ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ። 8የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድ​ሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሆ​ነው ሞተ። 9በተ​ራ​ራ​ማዉ በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን#ግእዙ “በመ​ስዕ” ይላል። ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት። 10ትው​ልድ ሁሉ ደግሞ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ተጨ​መሩ፤ ከእ​ነ​ዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን ሥራ ያላ​ወቀ ሌላ ትው​ልድ ተነሣ።
እስ​ራ​ኤል አም​ል​ኮተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መተ​ዋ​ቸው
11የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ በዓ​ሊ​ም​ንም አመ​ለኩ። 12ከግ​ብፅ ምድ​ርም ያወ​ጣ​ቸ​ውን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተዉ፤ ሌሎ​ች​ንም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አስ​ቈ​ጡት። 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትተው በዓ​ል​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተቈጣ፤ ወደ ማረ​ኳ​ቸ​ውም ማራ​ኪ​ዎች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ማረ​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ባሉት በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወዲያ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሊቋ​ቋሙ አል​ቻ​ሉም። 15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ እንደ ማለ፥ ወደ ወጡ​በት ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ትከ​ፋ​ባ​ቸው ነበ​ረች፤ እጅ​ግም ተጨ​ነቁ።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል መሳ​ፍ​ን​ትን እንደ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሳ​ፍ​ን​ትን አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው፤ ከሚ​ማ​ር​ኳ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ኗ​ቸው። 17ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ተከ​ት​ለው አመ​ነ​ዘሩ፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም እንጂ፥ መሳ​ፍ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አል​ሰ​ሙም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አስ​ቈ​ጡት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል እን​ዳ​ይ​ሰሙ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ይሄ​ዱ​ባት የነ​በ​ረ​ች​ውን መን​ገድ ፈጥ​ነው ተዉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም አላ​ደ​ረ​ጉም። 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሳ​ፍ​ን​ትን ባስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ስ​ፍኑ ጋር ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሚ​ዋ​ጉ​አ​ቸው ሰዎች ፊት ከመ​ከ​ራ​ቸው የተ​ነሣ ይቅር ብሏ​ቸ​ዋ​ልና በመ​ስ​ፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አዳ​ና​ቸው። 19መስ​ፍኑ ግን ከሞተ በኋላ ዳግ​መኛ ተመ​ል​ሰው ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ይልቅ እጅግ ይበ​ድሉ፤ ነበር፤ ሂደ​ውም ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ተከ​ት​ለው ያመ​ል​ኳ​ቸው ነበር፤ ይሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ነበር፤ ክፋ​ታ​ቸ​ው​ንም አይ​ተ​ዉም ነበር፤ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም አይ​መ​ለ​ሱም ነበር። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህ ሕዝብ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ያዘ​ዝ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ስለ ተላ​ለፉ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥ 21እኔም የነዌ ልጅ ኢያሱ ትቶ​አ​ቸው ከአ​ለፈ አሕ​ዛብ አን​ዱን ሰው እን​ኳን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከፊ​ታ​ቸው አላ​ወ​ጣም። 22አባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ጠበቁ፥ ይሄ​ዱ​ባት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ወይም አይ​ጠ​ብቁ እንደ ሆነ እስ​ራ​ኤ​ልን እፈ​ት​ን​ባ​ቸው ዘንድ፤” 23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ አስ​ቀረ፤ ፈጥ​ኖም አላ​ወ​ጣ​ቸ​ውም፤ በኢ​ያ​ሱም እጅ አሳ​ልፎ አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ