የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 11:30-34

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 11:30-34 አማ2000

ዮፍ​ታ​ሔም፥ “በእ​ው​ነት የአ​ሞ​ንን ልጆች በእጄ አሳ​ል​ፈህ ብት​ሰ​ጠኝ፥ ከአ​ሞን ልጆች ዘንድ በደ​ኅና በተ​መ​ለ​ስሁ ጊዜ፥ ከቤቴ ደጅ ወጥቶ የሚ​ቀ​በ​ለ​ኝን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ” ብሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ተሳለ። ዮፍ​ታ​ሔም ሊዋ​ጋ​ቸው ወደ አሞን ልጆች ተሻ​ገረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእጁ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። ከአ​ሮ​ዔ​ርም እስከ ሚኒ​ትና እስከ አቤ​ል​ክ​ራ​ሚም ድረስ ሃያ ከተ​ሞ​ችን በታ​ላቅ ሰልፍ አጠ​ፋ​ቸው። የአ​ሞ​ንም ልጆች በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ተዋ​ረዱ። ዮፍ​ታ​ሔም ወደ መሴፋ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ ልጁ ከበሮ ይዛ እየ​ዘ​ፈ​ነች ልት​ቀ​በ​ለው ወጣች፤ ለእ​ር​ሱም የሚ​ወ​ድ​ዳት አን​ዲት ብቻ ነበ​ረች። ከእ​ር​ስ​ዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አል​ነ​በ​ረ​ውም።