የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 31

31
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብ​ቃት
1ርዳታ ለመ​ፈ​ለግ ወደ ግብፅ ለሚ​ወ​ርዱ፥ በፈ​ረ​ሶ​ችና በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ለሚ​ታ​መኑ ወዮ​ላ​ቸው! ፈረ​ሰ​ኞቹ ብዙ​ዎች ናቸ​ውና፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ አል​ታ​መ​ኑ​ምና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ምና። 2እርሱ ግን ጠቢብ ነው፤ ክፉ​ንም ነገር በላ​ያ​ቸው ያመ​ጣል፤ ቃሉ​ንም አይ​መ​ል​ስም፤ በክ​ፉ​ዎ​ችም ሰዎች ቤት ላይ በከ​ንቱ ተስ​ፋ​ቸ​ውም ላይ ይነ​ሣል። 3ግብ​ፃ​ው​ያን ሰዎች እንጂ አም​ላክ አይ​ደ​ሉም፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ሥጋ እንጂ መን​ፈስ አይ​ደ​ሉም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ እጁን በዘ​ረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰ​ና​ከ​ላል፤ ተረ​ጂ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ ሁሉም በአ​ንድ ላይ ይጠ​ፋሉ።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛ​ልና፥ “አን​በሳ ወይም የአ​ን​በሳ ደቦል በን​ጥ​ቂ​ያው ላይ እን​ደ​ሚ​ያ​ገሣ፥ ድም​ፁም ተራ​ሮ​ችን እስ​ኪ​ሞላ በእ​ርሱ ላይ እን​ደ​ሚ​ጮህ፥ እረ​ኞ​ችም ሁሉ ሲጮ​ሁ​በት ከብ​ዛ​ታ​ቸው የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ፈራ፥ ከድ​ም​ፃ​ቸ​ውም የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ደ​ነ​ግጥ፥ እነ​ር​ሱም ከቍ​ጣው ብዛት የተ​ነሣ ድል እን​ደ​ሚ​ሆ​ኑና እን​ደ​ሚ​ደ​ነ​ግጡ፥ እን​ዲሁ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኮ​ረ​ብ​ታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወ​ር​ዳል። 5እን​ደ​ሚ​በ​ርር ወፍ እን​ዲሁ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይጋ​ር​ዳ​ታል፤ ይከ​ል​ላ​ታ​ልም፤ ይታ​ደ​ጋ​ታል፤ አል​ፎም ያድ​ና​ታል። 6ትበ​ድሉ ዘንድ ጥልቅ ምክ​ርን የም​ት​መ​ክሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ ተመ​ለሱ። 7በዚ​ያም ቀን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እጆ​ቻ​ቸው የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይጥ​ላሉ። 8አሦ​ርም ይወ​ድ​ቃል፤ የሚ​ወ​ድ​ቀ​ውም በሰው ሰይፍ አይ​ደ​ለም፤ የም​ት​በ​ላ​ቸ​ውም የሰው ሰይፍ አይ​ደ​ለ​ችም፤ የሚ​ሸ​ሹም ከሰ​ይፍ ፊት አይ​ደ​ለም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸው ግን ይሸ​ነ​ፋሉ። 9ዓለ​ትም ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች ድልም ይሆ​ናሉ የሸ​ሸም ይያ​ዛል። በጽ​ዮን ዘርእ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቤቶች ያሉት ብፁዕ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። #ዕብ. “እሳቱ በጽ​ዮን እቶ​ኑም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ይላል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ