የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሆሴዕ 5

5
ስለ ጣዖት አም​ልኮ የተ​ሰጠ ማስ​ጠ​ን​ቀ​ቂያ
1ካህ​ናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! አድ​ምጡ፤ የን​ጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድ​ርጉ፤ ለሚ​መ​ለ​ከት ወጥ​መድ፥ በታ​ቦ​ርም ላይ የተ​ዘ​ረጋ አሽ​ክላ ሆና​ች​ኋ​ልና ፍርድ በእ​ና​ንተ ላይ ነው። 2የሚ​ያ​ድኑ አዳ​ኞች ያጠ​ም​ዱ​ባት ዘንድ ተከ​ሏት፤ እኔ ግን መካ​ሪ​ያ​ችሁ ነኝ።#ዕብ. “ዐመ​ፀ​ኞች ዕርድ አብ​ዝ​ተ​ዋል” ይላል። 3እኔ ኤፍ​ሬ​ምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከእኔ አል​ራ​ቀም፤ ኤፍ​ሬም ዛሬ አመ​ን​ዝ​ሮ​አ​ልና፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ረክ​ሶ​አ​ልና። 4ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ይመ​ለሱ ዘንድ ልባ​ቸ​ውን አላ​ቀ​ኑም፤ የዝ​ሙት መን​ፈስ በው​ስ​ጣ​ቸው አለና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አላ​ወ​ቁ​ት​ምና። 5የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ትዕ​ቢት በፊቱ ይመ​ሰ​ክ​ራል፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤ​ልና ኤፍ​ሬም በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ይደ​ክ​ማሉ፤ ይሁ​ዳም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይደ​ክ​ማል። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለመ​ሻት ከበ​ጎ​ቻ​ቸ​ውና ከላ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ይሄ​ዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእ​ነ​ርሱ ተለ​ይ​ቶ​አ​ልና አያ​ገ​ኙ​ትም። 7ዲቃ​ሎ​ችን ልጆች ወል​ደ​ዋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከድ​ተ​ዋል፤ አሁ​ንም ኵብ​ኵባ እነ​ር​ሱ​ንና ርስ​ታ​ቸ​ውን ይበ​ላ​ቸ​ዋል።
ጦር​ነት በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል
8በኮ​ረ​ብታ ላይ መለ​ከ​ትን ንፉ፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ጩኹ፤ ብን​ያም በተ​ዋ​ረ​ደ​በት በቤ​ት​አ​ዌን ዐዋጅ ንገሩ።#ዕብ. “በጊ​ብዓ መለ​ከ​ትን፥ በራባ እን​ቢ​ል​ታን ንፉና፦ ብን​ያም ሆይ! ከአ​ንተ በኋላ እያ​ላ​ችሁ በቤት አዊን ላይ እሪ በሉ” ይላል። 9ኤፍ​ሬም በዘ​ለፋ ቀን ለጥ​ፋት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች የታ​መ​ነ​ውን ነገር አሳ​የሁ። 10የይ​ሁዳ አለ​ቆች ድም​በ​ርን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ርሱ ሆነ​ዋል፤ እኔም መዓ​ቴን እንደ ውኃ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ። 11ኤፍ​ሬም የተ​ገፋ ሆነ፤ በፍ​ር​ድም ተረ​ገጠ፤ ከን​ቱን ይከ​ተል ዘንድ ጀም​ሮ​አ​ልና። 12እኔም ለኤ​ፍ​ሬም እንደ ብል፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሀከክ” ይላል። ለይ​ሁ​ዳም ቤት እንደ ነቀዝ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቀኖት” ይላል። እሆ​ን​በ​ታ​ለሁ። 13ኤፍ​ሬ​ምም ደዌ​ውን አያት፤ ይሁ​ዳም ሥቃ​ዩን አያት፤ ኤፍ​ሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወደ ኢያ​ሪም መል​እ​ክ​ተ​ኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈ​ው​ሳ​ችሁ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ከእ​ና​ን​ተም ሕማም አል​ተ​ወ​ገ​ደም። 14እኔም ለኤ​ፍ​ሬም እንደ ነብር፥ ለይ​ሁ​ዳም ቤት እንደ አን​በሳ ደቦል እሆ​ና​ለ​ሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እወ​ስ​ድ​ማ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸ​ውም የለም። 15እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥#ዕብ. “በደ​ላ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ውቁ ድረስ” ይላል። ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ