የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 9:11-15

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 9:11-15 አማ2000

ክር​ስ​ቶስ ግን ለም​ት​መ​ጣ​ይቱ መል​ካም ነገር ሊቀ ካህ​ናት ሆኖ፥ የሰው እጅ ወደ አል​ሠ​ራት፥ በዚህ ዓለም ወደ አል​ሆ​ነ​ችው፥ ከፊ​ተ​ኛ​ዪቱ ወደ​ም​ት​በ​ል​ጠ​ውና ወደ​ም​ት​ሻ​ለው ድን​ኳን፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም መድ​ኀ​ኒ​ትን ገን​ዘብ አድ​ርጎ፥ በገዛ ደሙ አንድ ጊዜ ወደ መቅ​ደስ ገባ እንጂ በላ​ምና በፍ​የል ደም አይ​ደ​ለም። የላ​ምና የፍ​የል ደም፥ በረ​ከ​ሱ​ትም ላይ የሚ​ረጭ የጊ​ደር አመድ፥ የሚ​ያ​ነ​ጻና የረ​ከ​ሱ​ት​ንም ሥጋ​ቸ​ውን የሚ​ቀ​ድ​ሳ​ቸው ከሆነ፥ ነውር የሌ​ለው ሆኖ፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም መን​ፈስ ራሱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረበ የክ​ር​ስ​ቶስ ደም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ከው ዘንድ ሕሊ​ና​ች​ንን ከሞት ሥራ እን​ዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን? ስለ​ዚህ ኢየ​ሱስ ሞትን ተቀ​ብሎ፥ በቀ​ደ​መው ሥር​ዐት ስተው የነ​በ​ሩ​ትን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ወደ ዘለ​ዓ​ለም ርስ​ቱም የጠ​ራ​ቸው ተስ​ፋ​ውን ያገኙ ዘንድ፥ ለአ​ዲ​ሲቱ ኪዳን መካ​ከ​ለኛ ሆነ።