የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 5:1-8

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 5:1-8 አማ2000

የሰ​ዎች የት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ይህ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዳ​ምን በፈ​ጠረ ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሳሌ አደ​ረ​ገው፤ ወን​ድና ሴት አድ​ርጎ ፈጠ​ራ​ቸው፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም። እነ​ር​ሱ​ንም በፈ​ጠ​ረ​በት ቀን ስሙን አዳም ብሎ ጠራው። አዳ​ምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅ​ንም እንደ ምሳ​ሌው እንደ መልኩ ወለደ፤ ስሙ​ንም ሴት ብሎ ጠራው። አዳ​ምም ሴትን ከወ​ለደ በኋላ የኖ​ረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። አዳ​ምም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም። ሴትም ሁለት መቶ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ሄኖ​ስ​ንም ወለደ፤ ሴትም ሄኖ​ስን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። ሴትም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}