ዘፍጥረት 5:1-8
ዘፍጥረት 5:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የሰዎች የትውልድ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸውም። እነርሱንም በፈጠረበት ቀን ስሙን አዳም ብሎ ጠራው። አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅንም እንደ ምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው። አዳምም ሴትን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም። ሴትም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፤ ሄኖስንም ወለደ፤ ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። ሴትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
ዘፍጥረት 5:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የተጻፈው የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው በራሱ አምሳል አበጀው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ባረካቸው፤ በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው” ብሎ ጠራቸው፦ አዳም፣ ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን ራሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው። ሴት ከተወለደም በኋላ፣ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ። ሴት፣ ዕድሜው 105 ዓመት ሲሆን ሄኖስን ወለደ፤ ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ሴት በአጠቃላይ 912 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
ዘፍጥረት 5:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው። አዳምም ሴትን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወስደ። አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ሞተም። ሴትም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፤ ሄኖስንም ወለደ፤ ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ሴትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥራ ሁለት ዓመት ሆነ ሞተም።
ዘፍጥረት 5:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የአዳም የዘር ሐረግ ከዚህ የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረ ጊዜ በራሱ አምሳያ ፈጠራቸው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸው፤ “ሰው” ብሎም ሰየማቸው። አዳም መቶ ሠላሳ ዓመት በሆነው ጊዜ በመልኩና በአምሳያው እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ “ሤት” የሚል ስምም አወጣለት። ከዚህ በኋላ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 930 ዓመት ሲሆነውም ሞተ። ሴት 105 ዓመት ሲሆነው ሄኖስን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ ሴት 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 912 ዓመት ሲሆነውም ሞተ።
ዘፍጥረት 5:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የአዳም የዘር ሐረግ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረ ጊዜ በእግዚአብሔር አምሳያ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው” ብሎ ጠራቸው። አዳምም መቶ ሠላሳ ዓመት ሲኖር፥ እሱን የሚመስል፥ አምሳያው የሆነ፥ የልጅ አባት ሆነ፤ ሤት ብሎም ስም አወጣለት። ሤትንም ከወለደ በኋላ አዳም ስምንት መቶ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ሤትም አንድ መቶ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሄኖስንም ወለደ፤ ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሤት ስምንት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ሤትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፥ ሞተም።