ዮሴፍም ገባ፤ ለፈርዖንም እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “አባቴና ወንድሞች በጎቻቸውም፥ ላሞቻቸውም፥ ያላቸውም ሁሉ ከከነዓን ምድር መጡ፤ እነርሱም እነሆ፥ ወደ ጌሤም ምድር ደረሱ።” ከወንድሞቹም አምስት ሰዎችን ወስዶ በፈርዖን ፊት አቆማቸው። ፈርዖንም የዮሴፍን ወንድሞች፥ “ሥራችሁ ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፥ “እኛ አገልጋዮችህ፥ አባታችንም ከብት ጠባቂዎች ነን” አሉት። ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፥ “በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን፤ የአገልጋዮችህ በጎች የሚሰማሩበት ስፍራ የለምና፤ ራብም በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶአልና፤ አሁንም አገልጋዮችህ በጌሤም ምድር እንቀመጥ።” ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ ብሎ ተናገረው፥ “አባትህና ወንድሞችህ መጥተውልሃል፤ እነሆ፥ የግብፅ ምድር በፊትህ ናት፤ በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው፤ ከእነርሱም ውስጥ ዕውቀት ያላቸውን ሰዎች ታውቅ እንደሆነ በእንስሶች ጠባቂዎች ላይ አለቆች አድርጋቸው።” ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው። ፈርዖንም ያዕቆብን፥ “የኖርኸው ዘመን ስንት ነው?” አለው። ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፥ “በእንግድነት የኖርሁት የሕይወቴ ዘመንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕይወቴም ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ሆኑብኝ፤ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።” ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው፤ ከፈርዖንም ፊት ወጣ። ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ፤ ፈርዖን እንዳዘዘላቸውም በግብፅ ምድር በተሻለችው በራምሴ ምድር ርስትን ሰጣቸው። ዮሴፍም ለአባቱና ለወንድሞቹ፥ ለአባቱም ቤተ ሰዎች ሁሉ ለእያንዳንዱ ሰው እየሰፈረ እህልን ለምግብ ይሰጣቸው ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 47 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 47:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች