የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 45

45
ዮሴፍ ራሱን ለወ​ን​ድ​ሞቹ መግ​ለጡ
1ዮሴ​ፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታ​ገሥ አል​ተ​ቻ​ለ​ውም፥ “ሰዎ​ቹ​ንም ሁሉ ከፊቴ አስ​ወ​ጡ​ልኝ” ብሎ ተና​ገረ፤ ዮሴፍ ለወ​ን​ድ​ሞቹ ራሱን በገ​ለጠ ጊዜ በእ​ርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አል​ነ​በ​ረም። 2ቃሉ​ንም ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ፤ የግ​ብፅ ሰዎ​ችም ሰሙ፤ በፈ​ር​ዖን ቤትም ተሰማ። 3ዮሴ​ፍም ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ “እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕ​ይ​ወቱ ነውን?” አላ​ቸው። ወን​ድ​ሞ​ቹም ይመ​ል​ሱ​ለት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ ደን​ግ​ጠው ነበ​ርና። 4ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላ​ቸው። ወደ እር​ሱም ቀረቡ። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ግብፅ የሸ​ጣ​ች​ሁኝ እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ። 5አሁ​ንም ወደ​ዚህ ስለ​ሸ​ጣ​ች​ሁኝ አት​ፍሩ፤ አት​ቈ​ር​ቈ​ሩም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ይ​ወት ከእ​ና​ንተ በፊት ልኮ​ኛ​ልና። 6እነሆ፥ ይህ ሁለቱ ዓመት በም​ድር ላይ ራብ የሆ​ነ​በት ነውና፤ የማ​ይ​ታ​ረ​ስ​በ​ትና የማ​ይ​ታ​ጨ​ድ​በት አም​ስት ዓመት ገና አለ። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ እን​ድ​ት​ድ​ኑና እን​ድ​ት​ተ​ርፉ እመ​ግ​ባ​ችሁ ዘንድ ከእ​ና​ንተ በፊት ላከኝ። 8አሁ​ንም እና​ንተ ወደ​ዚህ የላ​ካ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከኝ እንጂ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እንደ አባት#ግእዙ “ልጅ” ይላል። አደ​ረ​ገኝ፤ በቤ​ቱም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ላይ አለቃ አደ​ረ​ገኝ። 9አሁ​ንም ፈጥ​ና​ችሁ ወደ አባቴ ሂዱ፤ እን​ዲ​ህም በሉት፦ ልጅህ ዮሴፍ የሚ​ለው ነገር ይህ ነው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደ​ረ​ገኝ፤ ወደ እኔ ና፤ በዚ​ያም አት​ዘ​ግይ፤ 10በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም ምድ​ርም ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ ወደ እኔም ትቀ​ር​ባ​ለህ። አን​ተና ልጆ​ችህ የል​ጆ​ች​ህም ልጆች፥ በጎ​ች​ህና ላሞ​ችህ፥ የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ፥ 11በዚ​ያም አን​ተና የቤ​ትህ ሰዎች የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ እን​ዳ​ት​ቸ​ገሩ እመ​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የራቡ ዘመን ገና አም​ስት ዓመት ቀር​ቶ​አ​ልና፤ 12እነ​ሆም፥ ለእ​ና​ንተ እኔ ራሴ በአፌ እንደ ተና​ገ​ር​ሁ​አ​ችሁ እና​ንተ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ወን​ድሜ ብን​ያም በዐ​ዓ​ይ​ኖቹ አይ​ቶ​አል። 13ለአ​ባቴ በግ​ብፅ ምድር ያለ​ኝን ክብ​ሬን ሁሉ፥ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ት​ንም ሁሉ ንገ​ሩት፤ አባ​ቴ​ንም ወደ​ዚህ ፈጥ​ና​ችሁ አም​ጡት።” 14የወ​ን​ድ​ሙን የብ​ን​ያ​ም​ንም አን​ገት አቅፎ አለ​ቀሰ፤ ብን​ያ​ምም በአ​ን​ገቱ ላይ አለ​ቀሰ። 15ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ ሳማ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድ​ሞቹ ከእ​ርሱ ጋር ተጨ​ዋ​ወቱ።
16በፈ​ር​ዖ​ንም ቤት፥ “የዮ​ሴፍ ወን​ድ​ሞች መጡ” ተብሎ ወሬ ተሰማ፤ ፈር​ዖ​ንና ቤተ ሰቡም ሁሉ ደስ አላ​ቸው። 17ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “ለወ​ን​ድ​ሞ​ችህ እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ይህን አድ​ርጉ፤ ዕቃ​ች​ሁን ጭና​ችሁ ወደ ከነ​ዓን ምድር ሂዱ፤ 18አባ​ታ​ች​ሁ​ንና ንብ​ረ​ታ​ች​ሁን ሁሉ#ዕብ. “ቤተ ሰባ​ች​ሁን” ይላል። ይዛ​ችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም የግ​ብ​ፅን ምድር በረ​ከት ሁሉ እሰ​ጣ​ች​ሁ​አ​ለሁ፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ድልብ ትበ​ላ​ላ​ችሁ። 19አን​ተም ወን​ድ​ሞ​ች​ህን፦ እን​ዲህ አድ​ርጉ በላ​ቸው፤ ከግ​ብፅ ምድር ለሕ​ፃ​ኖ​ቻ​ችሁ፥ ለሴ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሰረ​ገ​ሎ​ችን ውሰዱ፤ አባ​ታ​ች​ሁ​ንም ይዛ​ችሁ ኑ፤ 20ለዕ​ቃ​ች​ሁም ዐይ​ና​ችሁ ለአ​የ​ውም ሁሉ አታ​ስቡ፤ የግ​ብፅ በረ​ከት ሁሉ ለእ​ና​ንተ ነውና።”
21የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም እንደ አዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ፤ ዮሴ​ፍም የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን እንደ ነገ​ረው ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ለመ​ን​ገድ ስን​ቅን ሰጣ​ቸው፤ 22ለሁ​ሉም ሁለት ሁለት መለ​ወጫ ልብስ ሰጣ​ቸው፤ ለብ​ን​ያም ግን ሦስት መቶ ብርና አም​ስት መለ​ወጫ ልብስ ሰጠው። 23ለአ​ባ​ቱም እን​ደ​ዚሁ ላከ፤ ከግ​ብፅ በረ​ከት ሁሉ የተ​ጫኑ ዐሥር አህ​ዮ​ችን፥ ደግ​ሞም በመ​ን​ገድ ለአ​ባቱ ስንቅ የተ​ጫኑ ዐሥር በቅ​ሎ​ዎ​ችን። 24ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በመ​ን​ገድ እርስ በር​ሳ​ችሁ አት​ጣሉ።” 25እነ​ር​ሱም ከግ​ብፅ ሀገር ወጥ​ተው ሄዱ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ወደ አባ​ታ​ቸው ወደ ያዕ​ቆብ ደረሱ። 26እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕ​ይ​ወቱ ነው፤ እር​ሱም በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖ​አል።” ያዕ​ቆ​ብም ልቡ ደነ​ገጠ፤ አላ​መ​ና​ቸ​ው​ምም፤ 27እነ​ር​ሱም ዮሴፍ ያላ​ቸ​ውን፥ የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ው​ንም ነገር ሁሉ ነገ​ሩት፤ ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ዮሴፍ የላ​ካ​ቸ​ውን ሰረ​ገ​ሎች በአየ ጊዜ የአ​ባ​ታ​ቸው የያ​ዕ​ቆብ ልቡ፥ መን​ፈ​ሱም ታደሰ። 28እስ​ራ​ኤ​ልም፥ “ልጄ ዮሴፍ ገና በሕ​ይ​ወት ከሆነ ይህ ለእኔ ታላቅ ነገር ነው፤ ሳል​ሞት እን​ዳ​የው እሄ​ዳ​ለሁ” አለ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ