ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 42:6-9

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 42:6-9 አማ2000

ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እር​ሱም ለም​ድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች በመጡ ጊዜ በም​ድር ላይ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ሰገ​ዱ​ለት። ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ያ​ቸው ጊዜ ዐወ​ቃ​ቸው፤ እን​ደ​ማ​ያ​ው​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ክፉ ቃል​ንም ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “እና​ንተ ከወ​ዴት መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ከከ​ነ​ዓን ምድር እህል ልን​ሸ​ምት የመ​ጣን ነን” አሉት። ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን ዐወ​ቃ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ዮሴ​ፍም አይ​ቶት የነ​በ​ረ​ውን ሕልም ዐሰበ። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰላ​ዮች ናችሁ ፤ የሀ​ገ​ሩን ሁኔታ ልታዩ መጥ​ታ​ች​ኋል።”

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}