የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 40

40
ዮሴፍ የእ​ስ​ረ​ኞ​ችን ሕልም እንደ ተረ​ጐመ
1ከዚህ ነገር በኋ​ላም እን​ዲህ ሆነ፤ የግ​ብፅ ንጉሥ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ ጌታ​ቸ​ውን የግ​ብፅ ንጉ​ሥን በደሉ። 2ፈር​ዖ​ንም በሁ​ለቱ ሹሞች በጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎቹ አለ​ቃና በእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎቹ አለቃ ላይ ተቈጣ፤ 3በእ​ስር ቤት ውስ​ጥም ዮሴፍ ታስሮ በነ​በ​ረ​በት የግ​ዞት ስፍራ አጋ​ዛ​ቸው። 4የእ​ስር ቤቱ ዘበ​ኞች አለ​ቃም ለዮ​ሴፍ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ያገ​ለ​ግ​ላ​ቸው ነበር፤ በግ​ዞት ቤትም አንድ ዓመት ተቀ​መጡ። 5ሁለ​ቱም በአ​ን​ዲት ሌሊት ሕል​ምን አለሙ። በግ​ዞት ቤት የነ​በ​ሩት የግ​ብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ ሁለ​ቱም እየ​ራ​ሳ​ቸው ሕል​ምን አለሙ። 6ዮሴ​ፍም ማልዶ ወደ እነ​ርሱ ገባ፤ እነ​ሆም፥ አዝ​ነው አያ​ቸው። 7በጌ​ታው ቤት ከእ​ርሱ ጋር በግ​ዞት የነ​በ​ሩ​ት​ንም የፈ​ር​ዖን ሹሞች እን​ዲህ ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፥ “እና​ንት ዛሬ ስለ​ምን አዝ​ና​ች​ኋል?” 8እነ​ር​ሱም፥ “ሕል​ምን አል​መን የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ልን አጣን” አሉት። ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “ሕል​ምን የሚ​ተ​ረ​ጕም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠው አይ​ደ​ለ​ምን? እስቲ ንገ​ሩኝ፤ ሕል​ማ​ችሁ ምን​ድን ነው?”
9የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃም ለዮ​ሴፍ ሕል​ሙን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “በሕ​ልሜ የወ​ይን ሐረግ በፊቴ ሆና አየሁ፥ 10በሐ​ረ​ጉም ሦስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ወጡ፤ እር​ስ​ዋም ቅጠ​ልና አበባ አወ​ጣች፤ ዘለ​ላም አን​ጠ​ለ​ጠ​ለች፤ የዘ​ለ​ላ​ዋም ፍሬ በሰለ፤ 11የፈ​ር​ዖ​ንም ጽዋ በእጄ ነበር፤ ፍሬ​ው​ንም ወስጄ በፈ​ር​ዖን ጽዋ ጨመ​ቅ​ሁት፤ ጽዋ​ዉ​ንም ለፈ​ር​ዖን በእጁ ሰጠ​ሁት።” 12ዮሴ​ፍም አለው፥ “የሕ​ል​ምህ ትር​ጓ​ሜው ይህ ነው፤ ሦስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ሦስት ቀኖች ናቸው። 13እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ፈር​ዖን ሹመ​ት​ህን ያስ​ባል፤ ወደ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃ​ነ​ት​ህም ይመ​ል​ስ​ሃል፤ ጠጅ አሳ​ላፊ በነ​በ​ር​ህ​በት ጊዜ ስታ​ደ​ር​ገው እንደ ነበ​ረው እንደ ቀድ​ሞው ሹመ​ት​ህም የፈ​ር​ዖ​ንን ጽዋ በእጁ ትሰ​ጣ​ለህ። 14ነገር ግን በጎ ነገር በተ​ደ​ረ​ገ​ልህ ጊዜ እኔን ዐስ​በኝ፤ ምሕ​ረ​ት​ንም አድ​ር​ግ​ልኝ፤ ስለ እኔም ለፈ​ር​ዖን አሳ​ስ​በህ ከዚህ እስር ቤት አው​ጣኝ፤ 15ሌቦች በስ​ውር ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሀገር ሰር​ቀ​ው​ኛ​ልና፤ በዚ​ህም ደግሞ ምንም ያደ​ረ​ግ​ሁት ሳይ​ኖር በግ​ዞት ቤት አኑ​ረ​ው​ኛ​ልና።”
16የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎቹ አለ​ቃም ሕል​ሙን በመ​ል​ካም እንደ ተረ​ጐ​መ​ለት በአየ ጊዜ ዮሴ​ፍን እን​ዲህ አለው፥ “እኔም ደግሞ ሕልም አይች ነበር፤ እነ​ሆም፥ ሦስት መሶብ ነጭ እን​ጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤ 17በላ​ይ​ኛ​ውም መሶብ ፈር​ዖን የሚ​በ​ላው ጋጋ​ሪው በያ​ይ​ነቱ የሠ​ራው መብል ነበ​ረ​በት፤ ወፎ​ችም በራሴ ላይ ከመ​ሶቡ ይበሉ ነበር።” 18ዮሴ​ፍም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “የሕ​ል​ምህ ትር​ጓ​ሜው ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ 19እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈር​ዖን ራስ​ህን ይቈ​ር​ጥ​ሃል፤ በዕ​ን​ጨ​ትም ላይ ይሰ​ቅ​ል​ሃል፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችም ሥጋ​ህን ይበ​ሉ​ታል።” 20እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈር​ዖን የተ​ወ​ለ​ደ​በት ዕለት ነበር፤ ለሠ​ራ​ዊ​ቱም ሁሉ ግብር አደ​ረገ፤ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹን አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹን አለቃ በአ​ሽ​ከ​ሮቹ መካ​ከል ዐሰበ። 21የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ ወደ ሹመቱ መለ​ሰው፤ ጽዋ​ው​ንም በፈ​ር​ዖን እጅ ሰጠ፤ 22የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ በዕ​ን​ጨት ላይ ሰቀ​ለው፤ ዮሴፍ እንደ ተረ​ጐ​መ​ላ​ቸው። 23የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለቃ ግን ዮሴ​ፍን አላ​ሰ​በ​ውም፤ ረሳው እንጂ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ