የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 38:11-19

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 38:11-19 አማ2000

ይሁ​ዳም ምራ​ቱን ትዕ​ማ​ርን፥ “ልጄ ሴሎም እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በአ​ባ​ትሽ ቤት መበ​ለት ሆነሽ ተቀ​መጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወን​ድ​ሞቹ እን​ዳ​ይ​ሞ​ት​ብኝ ብሎ​አ​ልና። ትዕ​ማ​ርም ሄዳ በአ​ባቷ ቤት ተቀ​መ​ጠች። ዘመ​ን​ዋም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ የይ​ሁዳ ሚስት ሴዋ ሞተች፤ ይሁ​ዳም ተጽ​ናና፤ የበ​ጎ​ቹን ጠጕር ወደ​ሚ​ሸ​ል​ቱት ሰዎ​ችም ወደ ተምና ወጣ፤ እር​ሱም ዓዶ​ሎ​ማ​ዊው በግ ጠባ​ቂው ኤራ​ስም። ለም​ራቱ ትዕ​ማ​ርም፥ “እነሆ፥ አማ​ትሽ ይሁዳ የበ​ጎ​ቹን ጠጕር ይሸ​ልት ዘንድ ወደ ተምና ይወ​ጣል” ብለው ነገ​ሩ​አት። እር​ስ​ዋም የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ አወ​ለ​ቀች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም ለበ​ሰች፤ ተሸ​ፈ​ነ​ችም፤ ወደ ተም​ናም በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ዳር በኤ​ና​ይም ደጅ ተቀ​መ​ጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስ​ትም ትሆ​ነው ዘንድ እር​ስ​ዋን ሊሰ​ጠው እን​ዳ​ል​ፈ​ለገ አይ​ታ​ለ​ችና። ይሁ​ዳም በአ​ያት ጊዜ ዘማ መሰ​ለ​ችው፤ ፊቷን ተሸ​ፍና ነበ​ርና አላ​ወ​ቃ​ትም። ወደ እር​ስ​ዋም አዘ​ነ​በለ፥ “እባ​ክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት፤” እር​ስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላ​ወ​ቀም ነበ​ርና። እር​ስ​ዋም፥ “ወደ እኔ ብት​ገባ ምን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ?” አለ​ችው። “የፍ​የል ጠቦት ከመ​ን​ጋዬ እል​ክ​ል​ሻ​ለሁ” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “እስ​ክ​ት​ል​ክ​ልኝ ድረስ መያዣ ስጠኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “ምን መያዣ ልስ​ጥሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀለ​በ​ት​ህን፥ ኩፌ​ት​ህን፥ በእ​ጅህ ያለ​ውን በትር” አለች። እር​ሱም ሰጣ​ትና ከእ​ር​ስዋ ደረሰ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰ​ች​ለት። እር​ስ​ዋም ተነ​ሥታ ሄደች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም አው​ልቃ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ ለበ​ሰች።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}