የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 38

38
ይሁ​ዳና ትዕ​ማር
1በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ፤ ይሁዳ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ተለ​ይቶ ወረደ፤ ስሙ ኤራስ በሚ​ባል በዓ​ዶ​ሎ​ማ​ዊ​ውም ሰው ዘንድ አደረ። 2ከዚ​ያም ይሁዳ ያንድ ከነ​ዓ​ናዊ ሰው ሴት ልጅን አየ፤ ስም​ዋም ሴዋ#ዕብ. “ሴዋን” የይ​ሁዳ የሚ​ስቱ አባት ነው ይላል። ይባ​ላል። ወሰ​ዳ​ትም፤ ወደ እር​ስ​ዋም ገባ። 3ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ዔር ብላ ጠራ​ችው። 4ደግ​ሞም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም አው​ናን ብላ ጠራ​ችው። 5እን​ደ​ገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሴሎም ብላ ጠራ​ችው፤ እነ​ር​ሱ​ንም በወ​ለ​ደች ጊዜ ኬሴቢ በሚ​ባል ሀገር ነበ​ረች። 6ይሁ​ዳም ለበ​ኵር ልጁ ለዔር ትዕ​ማር የም​ት​ባል ሚስት አጋ​ባው። 7የይ​ሁ​ዳም የበ​ኵር ልጅ ዔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀሠ​ፈው። 8ይሁ​ዳም አው​ና​ንን፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ሚስት ግባ፤ አግ​ባ​ትም፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ዘርን አቁ​ም​ለት” አለው። 9አው​ና​ንም ዘሩ ለእ​ርሱ እን​ዳ​ይ​ሆን ዐወቀ፤ ወደ ወን​ድሙ ሚስ​ትም በገባ ጊዜ ለወ​ን​ድሙ ዘር እን​ዳ​ይ​ተካ ዘሩን በም​ድር ያፈ​ስ​ሰው ነበር። 10ይህም ሥራው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ክፉ ሆነ​በት፤ እን​ዲህ አድ​ር​ጎ​አ​ልና እር​ሱ​ንም ደግሞ ቀሠ​ፈው። 11ይሁ​ዳም ምራ​ቱን ትዕ​ማ​ርን፥ “ልጄ ሴሎም እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በአ​ባ​ትሽ ቤት መበ​ለት ሆነሽ ተቀ​መጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወን​ድ​ሞቹ እን​ዳ​ይ​ሞ​ት​ብኝ ብሎ​አ​ልና። ትዕ​ማ​ርም ሄዳ በአ​ባቷ ቤት ተቀ​መ​ጠች።
12ዘመ​ን​ዋም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ የይ​ሁዳ ሚስት ሴዋ ሞተች፤ ይሁ​ዳም ተጽ​ናና፤ የበ​ጎ​ቹን ጠጕር ወደ​ሚ​ሸ​ል​ቱት ሰዎ​ችም ወደ ተምና ወጣ፤ እር​ሱም ዓዶ​ሎ​ማ​ዊው በግ ጠባ​ቂው ኤራ​ስም። 13ለም​ራቱ ትዕ​ማ​ርም፥ “እነሆ፥ አማ​ትሽ ይሁዳ የበ​ጎ​ቹን ጠጕር ይሸ​ልት ዘንድ ወደ ተምና ይወ​ጣል” ብለው ነገ​ሩ​አት። 14እር​ስ​ዋም የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ አወ​ለ​ቀች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም ለበ​ሰች፤ ተሸ​ፈ​ነ​ችም፤ ወደ ተም​ናም በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ዳር በኤ​ና​ይም ደጅ ተቀ​መ​ጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስ​ትም ትሆ​ነው ዘንድ እር​ስ​ዋን ሊሰ​ጠው እን​ዳ​ል​ፈ​ለገ አይ​ታ​ለ​ችና። 15ይሁ​ዳም በአ​ያት ጊዜ ዘማ መሰ​ለ​ችው፤ ፊቷን ተሸ​ፍና ነበ​ርና አላ​ወ​ቃ​ትም። 16ወደ እር​ስ​ዋም አዘ​ነ​በለ፥ “እባ​ክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት፤” እር​ስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላ​ወ​ቀም ነበ​ርና። እር​ስ​ዋም፥ “ወደ እኔ ብት​ገባ ምን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ?” አለ​ችው። 17“የፍ​የል ጠቦት ከመ​ን​ጋዬ እል​ክ​ል​ሻ​ለሁ” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “እስ​ክ​ት​ል​ክ​ልኝ ድረስ መያዣ ስጠኝ” አለ​ችው። 18እር​ሱም፥ “ምን መያዣ ልስ​ጥሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀለ​በ​ት​ህን፥ ኩፌ​ት​ህን፥ በእ​ጅህ ያለ​ውን በትር” አለች። እር​ሱም ሰጣ​ትና ከእ​ር​ስዋ ደረሰ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰ​ች​ለት። 19እር​ስ​ዋም ተነ​ሥታ ሄደች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም አው​ልቃ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ ለበ​ሰች። 20ይሁ​ዳም መያ​ዣ​ውን ከሴ​ቲቱ እጅ ይቀ​በል ዘንድ በበግ ጠባ​ቂው በዓ​ዶ​ሎ​ማ​ዊው እጅ የፍ​የ​ሉን ጠቦት ላከ​ላት፤ እር​ስ​ዋ​ንም አላ​ገ​ኛ​ትም። 21እር​ሱም የሀ​ገ​ሩን ሰዎች፥ “በኤ​ና​ይም በመ​ን​ገድ ዳር ተቀ​ምጣ የነ​በ​ረች ዘማ ወዴት ናት?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “በዚህ ዘማ አል​ነ​በ​ረ​ችም” አሉት። 22ወደ ይሁ​ዳም ተመ​ልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አላ​ገ​ኘ​ኋ​ትም፤ የሀ​ገሩ ሰዎች ደግሞ፦ ከዚህ ዘማ የለ​ችም” አሉኝ። 23ይሁ​ዳም፥ “እኛ መዘ​በቻ እን​ዳ​ን​ሆን ትው​ሰ​ደው፤ እነሆ፥ የፍ​የ​ሉን ጠቦት ላክ​ሁ​ላት፤ አን​ተም አላ​ገ​ኘ​ሃ​ትም” አለ።
24እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከሦ​ስት ወር በኋላ ለይ​ሁዳ፥ “ምራ​ትህ ትዕ​ማር ሴሰ​ነች፤ እነሆ፥ በዝ​ሙት ፀነ​ሰች” ብለው ነገ​ሩት። ይሁ​ዳም፥ “አው​ጡ​አ​ትና በእ​ሳት ትቃ​ጠል” አለ። 25እር​ስ​ዋም ሲወ​ስ​ዱ​አት ወደ አማቷ እን​ዲህ ብላ ላከች፤ “ተመ​ል​ከት፦ ይህ ቀለ​በት፥ ይህ ኩፌት፥ ይህ በትር የማን ነው? ይህስ ፅንስ የማን ነው?” 26ይሁ​ዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕ​ማር እው​ነ​ተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎ​ምን አል​ሰ​ጠ​ኋ​ት​ምና” አለ። ትገ​ደል ማለ​ት​ንም ተወ፤#“ትገ​ደል ማለ​ት​ንም ተወ” በግ​እዝ ብቻ ነው። ደግ​ሞም አላ​ወ​ቃ​ትም። 27መው​ለ​ጃ​ዋም በደ​ረሰ ጊዜ እነሆ፥ መንታ ልጆች በሆ​ድዋ ነበሩ። 28ስት​ወ​ል​ድም አንዱ እጁን አወጣ፤ አዋ​ላ​ጂ​ቱም ቀይ ፈትል ወስዳ በእጁ አሰ​ረች፥ “ይህ መጀ​መ​ሪያ ይወ​ጣል” አለች። 29እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እጁን በመ​ለሰ ጊዜ እነሆ፥ ወን​ድሙ ወጣ፤ እር​ስ​ዋም፥ “ለምን ጥሰህ ወጣህ? ስትል ስሙን ፋሬስ” ብላ ጠራ​ችው። 30ከእ​ር​ሱም በኋላ ቀይ ፈትል በእጁ ያለ​በት ወን​ድሙ ወጣ፤ ስሙም ዛራ ተባለ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ