የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 37:1-12

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 37:1-12 አማ2000

ያዕ​ቆ​ብም አባቱ በስ​ደት በኖ​ረ​በት ሀገር በከ​ነ​ዓን ምድር ተቀ​መጠ። የያ​ዕ​ቆ​ብም ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ዮሴፍ ዐሥራ ሰባት ዓመት በሆ​ነው ጊዜ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር የአ​ባ​ቱን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር፤ እር​ሱም ከአ​ባቱ ሚስ​ቶች ከባ​ላና ከዘ​ለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላ​ቴና ነበረ፤ ዮሴ​ፍም የክ​ፋ​ታ​ቸ​ውን ወሬ ወደ አባ​ታ​ቸው ወደ እስ​ራ​ኤል ያመጣ ነበር። ያዕ​ቆ​ብም ዮሴ​ፍን ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወ​ድ​ደው ነበር፤ እርሱ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደው ነበ​ርና። በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ችም ቀሚስ አደ​ረ​ገ​ለት። ወን​ድ​ሞ​ቹም አባ​ታ​ቸው ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ እን​ደ​ሚ​ወ​ድ​ደው በአዩ ጊዜ ጠሉት፤ በሰ​ላም ይና​ገ​ሩ​ትም ዘንድ አል​ቻ​ሉም። ዮሴ​ፍም ሕል​ምን አለመ፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ነገ​ራ​ቸው። እር​ሱም አላ​ቸው፥ “እኔ ያለ​ም​ሁ​ትን ሕልም ስሙ፤ እነሆ፥ እኛ በእ​ርሻ መካ​ከል ነዶ ስና​ስር ነበ​ርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእ​ና​ን​ተም ነዶ​ዎች በዙ​ርያ ከብ​በው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።” ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ “በእኛ ላይ ልት​ነ​ግ​ሥ​ብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆ​ነን ይሆን?” አሉት። እን​ደ​ገ​ናም ስለ ሕል​ሙና ስለ ነገሩ የበ​ለጠ ጠሉት። ደግ​ሞም ሌላ ሕል​ምን አየ፤ ለአ​ባ​ቱና ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ነገ​ራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ደግሞ ሌላ ሕልም አለ​ምሁ፤ ሕል​ሙም እን​ዲህ ነው፦ ፀሐ​ይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋ​ክ​ብ​ትም ይሰ​ግ​ዱ​ልኝ ነበር።” አባ​ቱም ገሠ​ጸው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ይህ ያለ​ም​ኸው ሕልም ምን​ድን ነው? በውኑ እኔና እና​ትህ፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ህም መጥ​ተን በም​ድር ላይ እን​ሰ​ግ​ድ​ልህ ይሆን?” ወን​ድ​ሞ​ቹም ቀኑ​በት፤ አባቱ ግን ይህን ነገር በልቡ ይጠ​ብ​ቀው ነበር። ወን​ድ​ሞ​ቹም በሴ​ኬም የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን በጎች ይጠ​ብቁ ዘንድ ሄዱ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}