የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 36

36
የዔ​ሳው ትው​ልድ
(1ዜ.መ. 1፥34-37)
1ኤዶም የተ​ባ​ለው የዔ​ሳው ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። 2ዔሳው ከከ​ነ​ዓን ልጆች ሚስ​ቶ​ችን አገባ፤ የኬ​ጤ​ያ​ዊ​ውን የዔ​ሎን ልጅ ሐዳ​ሶን፥ የኤ​ው​ያ​ዊው የሴ​ቤሶ ልጅ ሐና የወ​ለ​ዳ​ትን ኤሌ​ባ​ማን፥ 3የይ​ስ​ማ​ኤ​ልን ልጅ የና​ቡ​አት እኅት ቤሴ​ሞ​ትን። 4ሐዳሶ ለእ​ርሱ ኤል​ፋ​ዝን ወለ​ደች፤ ቤሴ​ሞ​ትም ራጉ​ኤ​ልን ወለ​ደች፤ 5ኤሌ​ባ​ማም ዮሔ​ልን፥ ይጉ​ሜ​ልን፥ ቆሬ​ንም ወለ​ደች። በከ​ነ​ዓን ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የዔ​ሳው ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። 6ዔሳ​ውም ሚስ​ቶ​ቹን፥ ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንና ሴቶች ልጆ​ቹን፥ ቤተ ሰቡ​ንም ሁሉ፥ እን​ስ​ሶ​ቹ​ንም ሁሉ፥ በከ​ነ​ዓ​ንም ሀገር ያገ​ኘ​ውን ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ይዞ ከወ​ን​ድሙ ከያ​ዕ​ቆብ ፊት ከከ​ነ​ዓን ሀገር ሄደ። 7ከብ​ታ​ቸው ስለ​በዛ በአ​ን​ድ​ነት ይቀ​መጡ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ምድር ከከ​ብ​ታ​ቸው ብዛት የተ​ነሣ ልት​በ​ቃ​ቸው አል​ቻ​ለ​ችም። 8ዔሳ​ውም በሴ​ይር ተራራ ተቀ​መጠ፤ ዔሳ​ውም ኤዶም ነው።
9በሴ​ይር ተራራ የሚ​ኖሩ የኤ​ዶ​ማ​ው​ያን አባት የዔ​ሳው ትው​ል​ድም እን​ዲህ ነው። 10የዔ​ሳው ልጆች ስም ይህ ነው፤ የዔ​ሳው ሚስት የሐ​ዳሶ ልጅ ኤል​ፋዝ፤ የዔ​ሳው ሚስት የቤ​ሴ​ሞት ልጅ ራጉ​ኤል። 11የዔ​ሳው ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ቴማን፥ ኤሞር፥ ሳፍር፥ ጎቶን፥ ቄኔዝ። 12ቴም​ና​ሕም ለዔ​ሳው ልጅ ለኤ​ል​ፋዝ ዕቅ​ብት ነበ​ረች፤ አማ​ሌ​ቅ​ንም ለኤ​ል​ፋዝ ወለ​ደ​ች​ለት፤ የዔ​ሳ​ውም ሚስት የሐ​ዳሶ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። 13የዔ​ሳው ልጅ#“የዔ​ሳው ልጅ” በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። የራ​ጉ​ኤል ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሲም፥ ሞዛህ፤ እነ​ዚ​ህም የዔ​ሳው ሚስት የቤ​ሴ​ሞት ልጆች ናቸው። 14የሴ​ቤ​ጎን ልጅ የሐና ልጅ የዔ​ሳው ሚስት የኤ​ሌ​ባማ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ለዔ​ሳ​ውም ዮሔ​ልን፥ ዩጉ​ሜ​ልን፥ ቆሬን ወለ​ደች።
15የዔ​ሳው ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ የዔ​ሳው የበ​ኵር ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆች፤ ቴማን መስ​ፍን፥ ኦሜር መስ​ፍን፥ ሳፍር መስ​ፍን፥ ቄኔዝ መስ​ፍን፥ 16ቆሬ መስ​ፍን፥ ጎቶን መስ​ፍን፥ አማ​ሌቅ መስ​ፍን፤ በኤ​ዶም ምድር የኤ​ል​ፋዝ መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ዚህ የሓ​ዳሶ ልጆች ናቸው ። 17የዔ​ሳው ልጅ የራ​ጉ​ኤል ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ ናሖት መስ​ፍን፥ ዛራ መስ​ፍን፥ ሲን መስ​ፍን፥ ሞዛህ መስ​ፍን፤ በኤ​ዶም ምድር የራ​ጉ​ኤል ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም የዔ​ሳው ሚስት የቤ​ሴ​ሞት ልጆች ናቸው። 18የዔ​ሳው ሚስት የኤ​ሌ​ባማ ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ ዮሔል መስ​ፍን፥ ይጉ​ሜል መስ​ፍን፥ ቆሬ መስ​ፍን፤ የዔ​ሳው ሚስት የሐና ልጅ የኤ​ሌ​ባማ ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው። 19የዔ​ሳው ልጆ​ችና መስ​ፍ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ር​ሱም የኤ​ዶም ልጆች ናቸው።
የሴ​ይር ዘሮች
(1ዜ.መ. 1፥38-42)
20በዚ​ያች ሀገር የተ​ቀ​መጡ የሖ​ሪ​ያ​ዊው የሴ​ይር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሉጣን፥ ሦባን፥ ሳባቅ፥ አናም፥ 21ዲሶን፥ ኤሶር፥ ዲሳን፤ እነ​ዚህ በኤ​ዶም ምድር የሖ​ሪ​ያ​ዊው የሴ​ይር ልጆች መሳ​ፍ​ንት ናቸው። 22የሉ​ጣን ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ሖሪ፥ ሃማን ናቸው፤ የሉ​ጣ​ንም እኅት ትም​ናዕ ናት። 23የሦ​ባን ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ዓል​ዋን፥ ማኔ​ሐት፥ ኤቤል፥ ሳፋር፥ አው​ናም። 24የሳ​ባቅ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ኢኣ፥ ዓናን፤ ይህም ዓናን በም​ድረ በዳ የአ​ባ​ቱን የሳ​ባ​ቅን አህ​ዮች ሲጠ​ብቅ ፍል ውኃ​ዎ​ችን#በግ​እዙ “ያሜን” ይላል። ያገኘ ነው። 25የዓ​ናን ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ዲሶን፤ የዓ​ናን ሴት ልጅ ኤሌ​ባማ። 26የዲ​ሶ​ንም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሕም​ዳን፥ አስ​ባን፥ ቤዖር፥#“ቤዖር” በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። ይት​ራን፥ ክራን። 27የኤ​ሶር ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ከል​ሐን፥ ዛኦን፥ ዓቃን። 28የሪ​ሶን#በግ​እዙ “ዲሳን” ይላል። ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ዑሳ፥ አራን። 29የሖሪ መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ ሉጣን መስ​ፍን፥ ሦባን መስ​ፍን፥ ሳባቅ መስ​ፍን፥ ዓናን መስ​ፍን፥ 30ዲሶን መስ​ፍን፥ ኤሶር መስ​ፍን፥ ሪሶን መስ​ፍን፤ በሴ​ይር ምድር በየ​ሹ​መ​ታ​ቸው መሳ​ፍ​ንት የሆኑ የሖሪ መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው።
የኤ​ዶም ነገ​ሥ​ታት
(1ዜ.መ. 1፥43-54)
31በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመ​ን​ገሡ በፊት በኤ​ዶም ሀገር የነ​ገሡ ነገ​ሥ​ታት እነ​ዚህ ናቸው። 32በኤ​ዶ​ምም የቤ​ዖር ልጅ ባላቅ ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ዋም ስም ዴናባ ናት። 33ባላ​ቅም ሞተ፤ በእ​ርሱ ፈን​ታም የባ​ሶ​ራው የዛራ ልጅ ኢዮ​ባብ ነገሠ። 34ኢዮ​ባ​ብም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ የቴ​ማ​ኒው ሀገር ሑሳም ነገሠ። 35ሑሳ​ምም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ የም​ድ​ያ​ምን ሰዎች በሞ​ዓብ ሜዳ የገ​ደለ የቤ​ዳድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ዋም ስም ዓዊት ተባለ። 36ዓዳ​ድም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ የም​ስ​ሬ​ቃው ሠምላ ነገሠ። 37ሠም​ላም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ በወ​ንዝ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከር​ኆ​ቦት ሳኦል ነገሠ። 38ሳኦ​ልም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ የዓ​ክ​ቦር ልጅ በአ​ል​ሐ​ናን ነገሠ። 39የአ​ክ​ቦር ልጅ በአ​ል​ሐ​ና​ንም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ አዳር ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ውም ስም ፎጎር ነው፤ ሚስ​ቱም የሜ​ዛ​አብ ልጅ መጥ​ሬድ የወ​ለ​ደ​ቻት ምኤ​ጠ​ብ​ኤል ትባ​ላ​ለች።
40የዔ​ሳ​ውም የመ​ሳ​ፍ​ንቱ ስም በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው፥ በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው፥ በያ​ገ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው ይህ ነው፤ ትም​ናዕ መስ​ፍን፥ ዓልዋ መስ​ፍን፥ ኤቴት መስ​ፍን፥ 41ኤሌ​ባማ መስ​ፍን፥ ኤላ መስ​ፍን፥ ፊኖን መስ​ፍን፥ 42ቄኔዝ መስ​ፍን፥ ቴማን መስ​ፍን፥ ሜብ​ሳር መስ​ፍን፥ 43መግ​ዴ​ኤል መስ​ፍን፥ ኤራም መስ​ፍን፤ እነ​ዚህ በግ​ዛ​ታ​ቸው ምድር በየ​መ​ኖ​ሪ​ያ​ቸው የኤ​ዶም መሳ​ፍ​ንት ናቸው። የኤ​ዶ​ማ​ው​ያ​ንም አባት ይህ ዔሳው ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ