አራንም ሎጥን ወለደ። አራንም በተወለደባት ሀገር በከለዳውያን ምድር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ። አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፤ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የናኮርም ሚስት የአራን ልጅ ሚልካ ናት፤ አራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነው። ሦራም መካን ነበረች፤ ልጆችም አልነበሩአትም። ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የአራንን ልጅ ሎጥን፥ የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ምድር አወጣቸው። ወደ ካራንም መጡ፤ በዚያም ተቀመጡ። ታራም በካራን ምድር የኖረበት ዘመን ሁለት መቶ አምስት ዓመት ሆነ፤ ታራም በካራን ሞተ።
ኦሪት ዘፍጥረት 11 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 11:27-32
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos