ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 11:11-30

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 11:11-30 አማ2000

ሴምም አር​ፋ​ክ​ስ​ድን ከወ​ለደ በኋላ አም​ስት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም። አር​ፋ​ክ​ስ​ድም መቶ ሠላሳ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ቃይ​ና​ን​ንም ወለደ፤ አር​ፋ​ክ​ስ​ድም ቃይ​ና​ንን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም። ቃይ​ና​ንም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ሳላ​ንም ወለደ፤ ቃይ​ና​ንም ሳላን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ልጆች ወለደ፤ ሞተም። ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ዔቦ​ር​ንም ወለደ፤ ሳላም ዔቦ​ርን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም። ዔቦ​ርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፤ ፋሌ​ቅ​ንም ወለደ፤ ዔቦ​ርም ፋሌ​ቅን ከወ​ለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም። ፋሌ​ቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ራግ​ው​ንም ወለደ፤ ፋሌ​ቅም ራግ​ውን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም። ራግ​ውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሴሮ​ሕ​ንም ወለደ፤ ራግ​ውም ሴሮ​ሕን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም። ሴሮ​ሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ናኮ​ር​ንም ወለደ፤ ሴሮ​ሕም ናኮ​ርን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም። ናኮ​ርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ታራ​ንም ወለደ፤ ታራ​ንም ከወ​ለደ በኋላ ናኮር መቶ ሀያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም። ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብ​ራ​ም​ንና ናኮ​ርን፥ አራ​ን​ንም ወለደ። አራ​ንም ሎጥን ወለደ። አራ​ንም በተ​ወ​ለ​ደ​ባት ሀገር በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በአ​ባቱ በታራ ፊት ሞተ። አብ​ራ​ምና ናኮ​ርም ሚስ​ቶ​ችን አገቡ፤ የአ​ብ​ራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የና​ኮ​ርም ሚስት የአ​ራን ልጅ ሚልካ ናት፤ አራ​ንም የሚ​ል​ካና የዮ​ስካ አባት ነው። ሦራም መካን ነበ​ረች፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}