የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ገላ​ትያ ሰዎች 6

6
ወን​ድ​ምን ስለ ማጽ​ና​ናት
1ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የተ​ሳ​ሳተ ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጸ​ና​ችሁ እና​ንት እን​ዳ​ት​ሳ​ሳቱ ለራ​ሳ​ችሁ እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሰው ቅን​ነት ባለው ልቡና አጽ​ኑት። 2ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውን ሸክም ይሸ​ከም፤ በዚ​ህም የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሕግ ትፈ​ጽ​ማ​ላ​ችሁ። 3አን​ዱም ምንም ሳይ​ሆን ምንም የሆነ ቢመ​ስ​ለው ራሱን ያታ​ል​ላ​ልና።#ግእዙ “አልቦ ዘያ​ስ​ሕት ርእሶ” ይላል። 4ለሌላ ያይ​ደለ ለራሱ መመ​ኪያ እን​ዲ​ሆ​ነው ሁሉም ሥራ​ዉን ይመ​ር​ምር። 5ሁሉም ሸክ​ሙን ይሸ​ከ​ማ​ልና።
6ይህ​ንም ነገር ንኡሰ ክር​ስ​ቲ​ያን ይስ​ማው፤ መል​ካ​ሙ​ንም ነገር ሁሉ ከሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረው ይማር። 7አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ዘ​ብት አይ​ኑር፤ ሰውም የሚ​ዘ​ራ​ውን ያጭ​ዳል። 8በሥ​ጋው የሚ​ዘራ ሞትን ያጭ​ዳል፤ በመ​ን​ፈ​ሱም የሚ​ዘራ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ያጭ​ዳል። 9በጎ ሥራ መሥ​ራ​ትን ቸል አን​በል፥#ግሪኩ “ባን​ዝ​ልም” የሚል አለው። በጊ​ዜው እና​ገ​ኘ​ዋ​ለ​ንና። 10እን​ግ​ዲህ ጊዜ ሳለን ለሁሉ መል​ካም ሥራ እና​ድ​ርግ፤ ይል​ቁ​ንም ለሃ​ይ​ማ​ኖት ሰዎች።
ምክ​ርና ቡራኬ
11በእጄ እንደ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ እዩ።#ግሪኩ “እን​ዴት ባሉ ታላ​ላቅ ፊደ​ላት እን​ደ​ጻ​ፍ​ሁ​ላ​ችሁ ...” ይላል። 12ለሰው ፊት ሊያ​ደሉ የሚ​ወዱ እነ​ዚያ እን​ድ​ት​ገ​ዘሩ ያስ​ገ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን መስ​ቀል እን​ዳ​ት​ከ​ተሉ ነው።#ግሪኩ “ስለ ክር​ስ​ቶስ መስ​ቀል እን​ዳ​ይ​ሰ​ደዱ ነው” ይላል። 13የተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም ቢሆኑ በሰ​ው​ነ​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​መኩ ልት​ገ​ዘሩ ይወ​ዳሉ እንጂ ኦሪ​ትን አል​ጠ​በ​ቁም። 14እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መስ​ቀል እንጂ በሌላ አል​መ​ካም፤ በእኔ ዘንድ ዓለሙ የሞተ ነው፥ እኔም በዓ​ለሙ ዘንድ የሞ​ትሁ ነኝ።#ግሪኩ “ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተ​ሰ​ቀ​ለ​በት፥ እኔም ለዓ​ለም የተ​ሰ​ቀ​ል​ሁ​በት ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መስ​ቀል በቀር ሌላ ትም​ክ​ሕት ከእኔ ይራቅ” ይላል። 15በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ አዲስ ፍጥ​ረት መሆን ነው እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ምም። 16ይህን ሕግ ለሚ​ፈ​ጽሙ ሰዎች ሰላ​ምና ይቅ​ርታ ይሁን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገ​ኖች በሆኑ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይም ይሁን።
17እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ የሚ​ያ​ደ​ክ​መኝ አይ​ኑር፤ እኔ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን መከራ#ግሪኩ “የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ማሕ​ተም” ይላል። በሥ​ጋዬ እሸ​ከ​ማ​ለሁ። 18ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።
በሮሜ ተጽፋ በቲቶ እጅ ወደ ገላ​ትያ ሰዎች የተ​ላ​ከች መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች።
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን፤ አሜን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ