የይሁዳና የብንያምም ጠላቶች፥ የምርኮኞቹ ልጆች ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መቅደስ እንደሚሠሩ ሰሙ። ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች ቤቶች አለቆችም ቀርበው፥ “የአሦር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ካመጣን ቀን ጀምሮ ለአምላካችሁ እንሠዋለንና፥ እንደ እናንተም እንፈልገዋለንና ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሉአቸው። ዘሩባቤልና ኢያሱም፥ የቀሩትም የእስራኤል አባቶች ቤቶች አለቆች፥ “የአምላካችንን ቤት መሥራት ለእኛና ለእናንተ አይደለም፤ እኛ ራሳችን ግን የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዳዘዘን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ቤት እንሠራለን” አሉአቸው። የሀገሩም ሕዝብ የይሁዳን ሕዝብ እጅግ ያዳክሙ ነበር፤ እንዳይሠሩም ከለከሉአቸው፤ ምክራቸውንም ያፈርሱ ዘንድ በፋርሱ ንጉሥ በቂሮስ ዘመን ሁሉ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት ድረስ መካሪዎችን ገዙባቸው።
መጽሐፈ ዕዝራ 4 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ዕዝራ 4:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች