የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 36:25-36

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 36:25-36 አማ2000

ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ። አዲስ ልብ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ አዲስ መን​ፈ​ስ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ የድ​ን​ጋ​ዩ​ንም ልብ ከሥ​ጋ​ችሁ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ። መን​ፈ​ሴ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ በት​እ​ዛ​ዜም እን​ድ​ት​ሄዱ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ፍር​ዴ​ንም ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ ታደ​ር​ጉ​ት​ማ​ላ​ችሁ። ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ኋት ምድር ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ብም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ። ከር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እህ​ል​ንም እጠ​ራ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ው​ማ​ለሁ፤ ራብ​ንም አላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም። ደግ​ሞም የራ​ብን ስድብ ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እን​ዳ​ት​ሸ​ከሙ የዛ​ፍን ፍሬና የእ​ር​ሻ​ውን መከር አበ​ዛ​ለሁ። ክፉ​ውን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና መል​ካም ያይ​ደ​ለ​ውን ሥራ​ች​ሁ​ንም ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁና ስለ ርኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ራሳ​ች​ሁን ትጸ​የ​ፋ​ላ​ችሁ። ይህን የሠ​ራሁ ስለ እና​ንተ እን​ዳ​ይ​ደለ በእ​ና​ንተ ዘንድ የታ​ወቀ ይሁን፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ መን​ገ​ዳ​ችሁ እፈ​ሩና ተዋ​ረዱ። “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ በአ​ነ​ጻ​ኋ​ችሁ ጊዜ በከ​ተ​ሞች ሰዎ​ችን አኖ​ራ​ለሁ፤ ባድ​ማ​ዎ​ቹም ስፍ​ራ​ዎች ይሠ​ራሉ። ባድማ የነ​በ​ረች፥ በመ​ን​ገ​ደ​ኛም ሁሉ ዐይን ዘንድ ባድማ የነ​በ​ረች ምድር ትታ​ረ​ሳ​ለች። ሰዎ​ችም ባድማ የነ​በ​ረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆና​ለች፤ የፈ​ረ​ሱት፥ ባድማ የሆ​ኑት፥ የጠ​ፉ​ትም ከተ​ሞች ተመ​ሽ​ገ​ዋል፤ ሰውም የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ሆነ​ዋል ይላሉ። በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም የቀ​ሩት አሕ​ዛብ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ረ​ሱ​ትን ስፍ​ራ​ዎች እንደ ሠራሁ፥ ውድማ የሆ​ነ​ው​ንም እንደ ተከ​ልሁ ያው​ቃሉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፥ እኔም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።