ፈርዖንም ልኮ ሙሴንና አሮንን ጠራ፤ “አሁንም በደልሁ፤ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢአተኞች ነን። እንግዲህ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ የአምላክ ነጐድጓድ፥ በረዶውም፥ እሳቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለቅቃችኋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህ አትቀመጡም” አላቸው። ሙሴም፥ “ለፈርዖን ከከተማ በወጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱም ለእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ ነጐድጓዱ ጸጥ ይላል፤ በረዶውም፥ ዝናቡም ደግሞ አይወርድም። ነገር ግን አንተና ሹሞችህ እግዚአብሔር አምላክን ምንጊዜም እንደማትፈሩ አውቃለሁ” አለው። ተልባውና ገብሱ ተመታ፤ ገብሱ አሽቶ፥ ተልባውም አፍርቶ ነበርና። ስንዴውና አጃው ግን አልተመቱም፤ ገና ቡቃያ ነበሩና። ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ከከተማ ወጣ፤ እጁንም ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጐድጓዱም፥ በረዶውም ጸጥ አለ፤ ዝናቡም በምድር ላይ አላካፋም። ፈርዖንም ዝናቡ፥ በረዶውም፥ ነጐድጓዱም ጸጥ እንደ አለ በአየ ጊዜ በደልን ጨመረ፤ እርሱና ሹሞቹም ልባቸውን አደነደኑ። የፈርዖንም ልብ ጸና፤ እግዚአብሔርም በሙሴ አፍ እንደ ተናገረ የእስራኤልን ልጆች አልለቀቀም።
ኦሪት ዘፀአት 9 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፀአት 9:27-35
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች