ኦሪት ዘፀ​አት 31:12-15

ኦሪት ዘፀ​አት 31:12-15 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እኔ የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ ዘንድ ለልጅ ልጃ​ችሁ ምል​ክት ነውና ሰን​በ​ቴን ፈጽሞ ጠብቁ። ለእ​ና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰች ናትና ሰን​በ​ቴን ጠብቁ፤ የሚ​ያ​ረ​ክ​ሳ​ትም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ሥራ​ንም በእ​ር​ስዋ የሠራ ሰው ሁሉ ያች ነፍስ ከሕ​ዝ​ብዋ መካ​ከል ተለ​ይታ ትጥፋ። ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሥራ፤ ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ስች የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ናት፤ በሰ​ን​በት ቀን የሚ​ሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}