ኦሪት ዘፀአት 31
31
ደብተራ ኦሪትን የሠሩ ባስልኤልና ኤልያብ
(ዘፀ. 35፥30—36፥1)
1እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“እይ! ከይሁዳ ነገድ የሚሆን የሆር የልጅ ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠርቼዋለሁ። 3በሥራ ሁሉ ያስተውል ዘንድ በጥበብም፥ በማስተዋልም፥ በዕውቀትም የእግዚአብሔርን መንፈስ ሞላሁበት፤ 4የአናጺዎች አለቃ ይሆን ዘንድ ወርቅንና ብርን፥ ናስንም፥ ብጫና ሰማያዊ፥ እጥፍ ሆኖ የተፈተለ ነጭና ቀይ ሐርን#“ብጫና ሰማያዊ እጥፍ ሆኖ የተፈተለ ነጭና ቀይ ሐር” የሚለው በዕብ. የለም። ይሠራ ዘንድ፤ 5በሥራውም ሁሉ የሚደረገውን የድንጋይ ማለዘብን፥ ከዕንጨትም የሚጠረበውን ይሠራ ዘንድ። 6እኔም እነሆ፥ ከዳን ነገድ የሚሆን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ሰጠሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ዕውቅትን ሰጠሁ። 7የምስክሩን ድንኳን፥ የቃል ኪዳኑንም ታቦት፥ በእርሱም ላይ ያለውን የስርየት መክደኛውን፥ የድንኳኑንም ዕቃ ሁሉ፤ 8የዕጣን መሠዊያውን፥ ገበታውንም፥ ዕቃውንም፥ ከዕቃው ሁሉ የነጻውን መቅረዝ፥ 9ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያ፥ ዕቃውንም ሁሉ፥#“ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠ ዊያ ዕቃውንም ሁሉ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውንም፥ 10በክህነት እኔን የሚያገለግሉበትን የካህኑን የአሮንን ልብሰ ተክህኖና የልጆቹን ልብስ፥ 11የሚቀቡትን የቅብዐቱንም ዘይት፥ ለመቅደሱ የሚያጥኑትን ዕጣን እንዳዘዝሁህ ሁሉ ያድርጉ።”
የሰንበት ሕግ
12እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ 13“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ ዘንድ ለልጅ ልጃችሁ ምልክት ነውና ሰንበቴን ፈጽሞ ጠብቁ። 14ለእናንተ በእግዚአብሔር የተቀደሰች ናትና ሰንበቴን ጠብቁ፤ የሚያረክሳትም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፤ ሥራንም በእርስዋ የሠራ ሰው ሁሉ ያች ነፍስ ከሕዝብዋ መካከል ተለይታ ትጥፋ። 15ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ ሰባተኛዋ ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደስች የዕረፍት ሰንበት ናት፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል። 16የእስራኤልም ልጆች ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ቃል ኪዳን ዕረፍት ያደርጉ ዘንድ ሰንበትን ይጠብቁ። 17እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰባተኛውም ቀን ሥራውን ፈጽሞ ስላረፈ፥ በእኔና በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘለዓለም ምልክት ነው።”
18እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ ሁለቱን የምስክር ጽላት፥ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 31: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ