የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 25:16-22

ኦሪት ዘፀ​አት 25:16-22 አማ2000

በታ​ቦ​ቱም ውስጥ እኔ የም​ሰ​ጥ​ህን ምስ​ክር ታስ​ቀ​ም​ጣ​ለህ። ከጥሩ ወር​ቅም ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስ​ር​የት መክ​ደኛ ሥራ። ሁለት ኪሩ​ቤል ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሥራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ። ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ጋር አን​ዱን ኪሩብ በአ​ንድ ወገን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ በሌ​ላው ወገን አድ​ር​ገህ በአ​ንድ ላይ ትሠ​ራ​ዋ​ለህ፤ ሁለ​ቱ​ንም ኪሩ​ቤል እን​ዲሁ በሁ​ለት ወገን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ። ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ ይዘ​ረ​ጋሉ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ይሸ​ፍ​ናሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እርስ በርሱ ይተ​ያ​ያል፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ ስር​የት መክ​ደ​ኛው ይሁን። የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ እኔም የም​ሰ​ጥ​ህን ምስ​ክር በታ​ቦቱ ውስጥ ታኖ​ረ​ዋ​ለህ። በዚ​ያም እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ፥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁ​ለት ኪሩ​ቤል መካ​ከል፥ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ ሆኜ እነ​ጋ​ገ​ር​ሃ​ለሁ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}