የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 17

17
ውኃ ከዓ​ለት እንደ ፈለ​ቀ​ላ​ቸው
(ዘዳ. 20፥1-13)
1የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራ​ፊ​ድም ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም። 2ሕዝ​ቡም ሙሴን ተጣ​ሉት፥ “የም​ን​ጠ​ጣ​ውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣ​ሉ​ኛ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ለምን ትፈ​ታ​ተ​ና​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው። 3ሕዝ​ቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛ​ንና ልጆ​ቻ​ች​ንን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም በጥ​ማት ልት​ገ​ድል ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ። 4ሙሴም፦ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለዚህ ሕዝብ ምን ላድ​ርግ? በድ​ን​ጋይ ሊወ​ግ​ሩኝ ጥቂት ቀር​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።” 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በሕ​ዝቡ ፊት እለፍ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤ ወን​ዙ​ንም የመ​ታ​ህ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ይዘ​ሃት ሂድ። 6እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮ​ሬብ በዓ​ለት ላይ በፊ​ትህ እቆ​ማ​ለሁ፤ ዓለ​ቱ​ንም ትመ​ታ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ይጠጣ ዘንድ ከእ​ርሱ ውኃ ይወ​ጣል” አለው። ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዲሁ አደ​ረገ። 7ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክር​ክር፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ነውን? ወይስ አይ​ደ​ለም?” ሲሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑት የዚ​ያን ስፍራ ስም “መን​ሱት” ደግ​ሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው።
እስ​ራ​ኤል ዐማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ድል እንደ አደ​ረጉ
8ዐማ​ሌ​ቅም መጥቶ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋራ በራ​ፊድ ተዋጋ። 9ሙሴም ኢያ​ሱን፥ “ጐል​ማ​ሶ​ችን ለአ​ንተ ምረጥ፤ ሲነ​ጋም ወጥ​ተህ ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔም በተ​ራ​ራው ራስ ላይ እቆ​ማ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በትር በእጄ ናት” አለው። 10ኢያ​ሱም ሙሴ እንደ አለው አደ​ረገ፤ ወጥ​ቶም ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮን፥ ሖርም ወደ ኮረ​ብ​ታው ራስ ወጡ። 11እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአ​ነሣ ጊዜ እስ​ራ​ኤል ድል ያደ​ርግ ነበር ፤ እጁ​ንም በአ​ወ​ረደ ጊዜ ዐማ​ሌቅ ድል ያደ​ርግ ነበር። 12የሙሴ እጆች ግን ከብ​ደው ነበር፤ ድን​ጋ​ይም ወሰዱ፤ በበ​ታ​ቹም አኖሩ፤ እር​ሱም ተቀ​መ​ጠ​በት፤ አሮ​ንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆ​ቹን ይደ​ግፉ ነበር፤ ፀሐ​ይም እስ​ክ​ት​ገባ ድረስ እጆቹ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር። 13ኢያ​ሱም ዐማ​ሌ​ቅ​ንና ሕዝ​ቡን በሰ​ይፍ ስለት አሸ​ነፈ።
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የዐ​ማ​ሌ​ቅን ዝክር ከሰ​ማይ በታች ጨርሼ እደ​መ​ስ​ሳ​ለ​ሁና ይህን ለመ​ታ​ሰ​ቢያ በመ​ጽ​ሐፍ ጻፈው፤ በኢ​ያ​ሱም ጆሮ ተና​ገር” አለው። 15ሙሴም መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም “ምም​ሕ​ፃን”#ዕብ. “ይህ​ዊህ ንሲ” ይላል። ብሎ ጠራው፤ 16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ሰ​ወ​ረች እጅ ዐማ​ሌ​ቅን እስከ ልጅ ልጅ ይዋ​ጋ​ልና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ