ኦሪት ዘፀ​አት 16:4-20

ኦሪት ዘፀ​አት 16:4-20 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በሕጌ ይሄዱ ወይም አይ​ሄዱ እንደ ሆነ እኔ እን​ድ​ፈ​ት​ና​ቸው፥ እነሆ፥ ከሰ​ማይ እን​ጀ​ራን አዘ​ን​ብ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡም ወጥ​ተው ለዕ​ለት ለዕ​ለት የሚ​በ​ቃ​ቸ​ውን ይሰ​ብ​ስቡ። እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ያመ​ጡ​ትን ያዘ​ጋጁ፤ ዕለት ዕለ​ትም ከሚ​ለ​ቅ​ሙት ይልቅ ሁለት እጥፍ ይሁን” አለው። ሙሴና አሮ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ምድር እንደ አወ​ጣ​ችሁ ማታ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ጥዋት ታያ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​ትን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ በእ​ኛም ላይ የም​ታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ እኛ ምን​ድን ነን?” አሉ። ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​በ​ትን ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና በመሸ ጊዜ ትበሉ ዘንድ ሥጋን፥ በማ​ለ​ዳም ትጠ​ግቡ ዘንድ እን​ጀ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እኛም ምን​ድን ነን? ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይ​ደ​ለም” አለ። ሙሴም አሮ​ንን፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ፦ ‘ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅረቡ’ በል” አለው። አሮ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በተ​ና​ገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታ​ቸ​ውን አቀኑ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በደ​መ​ናው ታየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፦ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማን​ጐ​ራ​ጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ማለ​ዳም እን​ጀ​ራን ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።” እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በመሸ ጊዜ ድር​ጭ​ቶች መጡ፤ ሰፈ​ሩ​ንም ሸፈ​ኑት፤ በማ​ለ​ዳም በሰ​ፈሩ ዙሪያ ጠል ወድቆ ነበር። የወ​ደ​ቀው ጠል በአ​ለፈ ጊዜ፥ እነሆ፥ በመ​ሬት ላይ እንደ ውርጭ ነጭ ሆኖ ድን​ብ​ላል የሚ​መ​ስል ደቃቅ ነገር በም​ድረ በዳ ታየ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ዩት ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ምን​ድን ነው?” ተባ​ባሉ። ያ ምን እን​ደ​ሆነ አላ​ወ​ቁ​ምና። ሙሴም አላ​ቸው፥ “ትበሉ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጣ​ችሁ እን​ጀራ ይህ ነው። ታደ​ር​ጉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፦ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ለቤተ ሰቡ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ ጎሞር ይሰ​ብ​ስብ፤ እንደ ቤተ ሰቡ ቍጥር ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ በድ​ን​ኳኑ አብ​ረ​ውት ከሚ​ኖ​ሩት ጋር ይሰ​ብ​ስብ።” የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ አንዱ አብ​ዝቶ፥ አን​ዱም አሳ​ንሶ ሰበ​ሰበ። በጎ​ሞ​ርም በሰ​ፈ​ሩት ጊዜ እጅግ ለሰ​በ​ሰበ አል​ተ​ረ​ፈ​ውም፤ ጥቂ​ትም ለሰ​በ​ሰበ አል​ጐ​ደ​ለ​በ​ትም፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ለየ​ቤቱ ሰበ​ሰበ። ሙሴም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማንም ከእ​ርሱ አን​ዳች ለነገ አያ​ስ​ቀር” አላ​ቸው። ነገር ግን ሙሴን አል​ሰ​ሙ​ትም፤ አን​ዳ​ንድ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ለነገ አስ​ቀሩ፤ እር​ሱም ተላ፤ ሸተ​ተም፤ ሙሴም ተቈ​ጣ​ቸው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}