የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 13

13
በኵር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ መሆኑ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”
የቂጣ በዓል
3ሙሴም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ የወ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ትን ይህ​ችን ቀን ዐስቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ቦታ በበ​ረ​ታች እጅ አው​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና። ስለ​ዚህ የቦካ እን​ጀራ አት​ብሉ። 4እና​ንተ በዚች ቀን በሚ​ያ​ዝያ ወር ወጥ​ታ​ች​ኋ​ልና። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ና​ንተ ይሰ​ጣት ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ​ማ​ለ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ምድር፥ ወደ ከና​ኔ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኬጢ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ምድር በአ​ገ​ባ​ችሁ ጊዜ ይህ​ችን ሥር​ዐት በዚህ ወር አድ​ርጉ። 6ስድ​ስት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ሰባ​ተ​ኛ​ውም ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ይሆ​ናል። 7ሰባት ቀንም ሙሉ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ዘንድ እርሾ ያለ​በት እን​ጀራ አይ​ታይ፤ በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቻ​ችሁ ሁሉ እርሾ አይ​ኑር። 8በዚ​ያም ቀን፦ ‘ከግ​ብፅ በወ​ጣሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ስለ​አ​ደ​ረ​ገ​ልኝ ነው’ ስትል ለል​ጅህ ትነ​ግ​ረ​ዋ​ለህ። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ረ​ታች እጅ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ሃ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ በአ​ፍህ ይሆን ዘንድ በእ​ጅህ እንደ ምል​ክት፥ በዐ​ይ​ኖ​ች​ህም መካ​ከል እንደ መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ን​ልህ። 10ከቀን ወደ ቀን በየ​ጊ​ዜው ይህን ሕግ ጠብ​ቁት።
11“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ችህ እን​ደ​ማለ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር በአ​ገ​ባህ ጊዜ፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለአ​ንተ በሰ​ጠህ ጊዜ፥ 12ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ ለይ፤ ከመ​ን​ጋ​ህና ከከ​ብ​ት​ህም መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለ​ደው ተባት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሆ​ናል። 13የአ​ህ​ያ​ውን በኵር በበግ ትለ​ው​ጠ​ዋ​ለህ፤ ባት​ለ​ው​ጠው ግን ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ።#ዕብ. “በጠ​ቦት ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ ባቷ​ጀው ግን አን​ገ​ቱን ትሰ​ብ​ረ​ዋ​ለህ” ይላል። የሰ​ው​ንም በኵር ሁሉ ከል​ጆ​ችህ መካ​ከል ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ። 14እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምን​ድን ነው?’ ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ርቱ እጅ ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣን፤ 15ፈር​ዖ​ንም እኛን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ባለ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው በኵር ጀምሮ እስከ እን​ስሳ በኵር ድረስ በግ​ብፅ ምድር ያለ​ውን በኵር ሁሉ ገደለ፤ ስለ​ዚህ ወንድ ሆኖ ማሕ​ፀ​ንን የከ​ፈ​ተ​ውን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠ​ዋ​ለሁ፤ ነገር ግን የል​ጆ​ችን በኵር ሁሉ እዋ​ጃ​ለሁ።’ 16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በብ​ርቱ እጅ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ሃ​ልና በእ​ጅህ እንደ ምል​ክት ፥ ከዐ​ይ​ኖ​ች​ህም እን​ደ​ማ​ይ​ርቅ ነገር ይሁ​ን​ልህ።”
የደ​መና ዐም​ድና የእ​ሳት ዐምድ
17እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፈር​ዖን ሕዝ​ቡን በለ​ቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር መን​ገድ አል​መ​ራ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ሕዝቡ ሰል​ፉን በአየ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጸ​ጽ​ተው፥ ወደ ግብ​ፅም እን​ዳ​ይ​መ​ለስ” ብሎ​አ​ልና። 18ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን በዙ​ሪያ መን​ገድ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለ​ችው ምድረ በዳ መራ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ ከግ​ብፅ ምድር ወጡ። 19ሙሴም የዮ​ሴ​ፍን ዐጽም ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መጐ​ብ​ኘ​ትን በጐ​በ​ኛ​ችሁ ጊዜ ዐጽ​ሜን ውሰዱ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ከዚህ አውጡ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። 20የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ከሱ​ኮት ተጓዙ፤ በም​ድረ በዳ​ውም ዳር በኦ​ቶም#ዕብ. “ኤታም” ይላል። ሰፈሩ። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ገድ ሊያ​ሳ​ያ​ቸው ቀን በዐ​ምደ ደመና፥ ሌሊ​ትም በዐ​ምደ እሳት ይመ​ራ​ቸው ነበር። 22ዐምደ ደመ​ናው በቀን፥ ዐምደ እሳ​ቱም በሌ​ሊት ከሕ​ዝቡ ፊት ከቶ ፈቀቅ አላ​ለም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ