የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 6:12-16

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 6:12-16 አማ2000

ሰል​ፋ​ችሁ፦ ከጨ​ለማ ገዦች ጋርና ከሰ​ማይ በታች ካሉ ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ጋር ነው እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና። ስለ​ዚ​ህም በክፉ ቀን መቃ​ወም እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጋሻ ያዙ፤ እን​ድ​ት​ጸ​ኑም በሁሉ የተ​ዘ​ጋ​ጃ​ችሁ ሁኑ። እን​ግ​ዲህ ወገ​ባ​ች​ሁን በእ​ው​ነት ታጥ​ቃ​ችሁ ቁሙ፤ የጽ​ድ​ቅ​ንም ጥሩር ልበሱ። የሰ​ላም ወን​ጌል ኀይ​ል​ንም ተጫ​ም​ታ​ችሁ ቁሙ። ከዚ​ህም ሁሉ ጋር የሚ​ን​በ​ለ​በሉ የክ​ፉን ፍላ​ፃ​ዎች ሁሉ ማጥ​ፋት እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ም​ነ​ትን ጋሻ አንሡ።