ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 5:25-28

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 5:25-28 አማ2000

ወን​ዶ​ችም ክር​ስ​ቶስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን እንደ ወደ​ዳት፥ ራሱ​ንም ስለ እር​ስዋ ቤዛ አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላት ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይው​ደዱ። በውኃ ጥም​ቀ​ትና በቃሉ ይቀ​ድ​ሳ​ትና ያነ​ጻት ዘንድ፥ የነ​ጻ​ችና የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሆን ዘንድ እንጂ በላ​ይዋ እድ​ፈት ወይም ርኵ​ሰት እን​ዳ​ያ​ገ​ኝ​ባት፥ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ኑን ለእ​ርሱ የከ​በ​ረች ያደ​ር​ጋት ዘንድ፤ እን​ዲ​ሁም ወን​ዶች ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እንደ ራሳ​ቸው አድ​ር​ገው ይው​ደዱ፤ ሚስ​ቱ​ንም የወ​ደደ ራሱን ወደደ።