ዘወትርም ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና አቅርቡ። እግዚአብሔርን በመፍራት ለባልንጀሮቻችሁ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ። ሴቶችም ለጌታችን እንደሚታዘዙ ለባሎቻቸው ይታዘዙ። ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስዋ አዳኝዋም እንደ ሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና። ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትታዘዝ፥ እንዲሁም ሴቶች ለባሎቻቸው በሁሉ ይታዘዙ። ወንዶችም ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት፥ ራሱንም ስለ እርስዋ ቤዛ አድርጎ እንደ ሰጠላት ሚስቶቻቸውን ይውደዱ። በውኃ ጥምቀትና በቃሉ ይቀድሳትና ያነጻት ዘንድ፥ የነጻችና የተቀደሰች ትሆን ዘንድ እንጂ በላይዋ እድፈት ወይም ርኵሰት እንዳያገኝባት፥ ቤተ ክርስቲያኑን ለእርሱ የከበረች ያደርጋት ዘንድ፤ እንዲሁም ወንዶች ሚስቶቻቸውን እንደ ራሳቸው አድርገው ይውደዱ፤ ሚስቱንም የወደደ ራሱን ወደደ። ከቶ ሥጋውን መጥላት የሚቻለው የለም፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ መገባት መግቡ፤ ጠብቁም። እኛ የአካሉ ሕዋሳት ነንና። “ስለዚህም ወንድ አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር አንድ ይሆናል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ።” ይህም ምሥጢር ታላቅ ነው፤ እኔም ይህንኑ ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ እናገረዋለሁ። እንግዲያስ እናንተም ሁላችሁ እንዲሁ ሚስቶቻችሁን እንደ ራሳችሁ ውደዱ፥ ሴትም ባልዋን ትፍራው።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:20-33
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos