የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 1:15-21

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 1:15-21 አማ2000

ስለ​ዚ​ህም እኔ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ና​ች​ሁን፥ ቅዱ​ሳ​ን​ንም ሁሉ መው​ደ​ዳ​ች​ሁን ሰምቼ፥ ስለ እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማመ​ስ​ገ​ን​ንና በጸ​ሎ​ቴም እና​ን​ተን ማሰ​ብን አላ​ቋ​ረ​ጥ​ሁም። ይኸ​ውም የክ​ብር ባለ​ቤት የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ ዕው​ቀ​ቱ​ንም ይገ​ል​ጽ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ ዐይነ ልቡ​ና​ች​ሁ​ንም ያበ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ የተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት ተስ​ፋም ምን እንደ ሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም የር​ስቱ ክብር ባለ​ጸ​ግ​ነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ፥ በክ​ር​ስ​ቶስ እንደ አደ​ረ​ገው እንደ ከሃ​ሊ​ነቱ ታላ​ቅ​ነት በም​ና​ምን በእኛ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው የከ​ሃ​ሊ​ነቱ ጽናት ብዛት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ ነው። ከሙ​ታን ለይቶ ባስ​ነ​ሣው፥ በሰ​ማ​ይም በቀኙ ባስ​ቀ​መ​ጠው፥ ከመ​ላ​እ​ክት ሁሉ በላይ ከመ​ኳ​ን​ን​ትና ከኀ​ይ​ላት፥ ከአ​ጋ​እ​ዝ​ትና ከሚ​ጠ​ራ​ውም ስም ሁሉ በላይ፥ በዚህ ዓለም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በሚ​መ​ጣ​ውም ዓለም እንጂ።