የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 12

12
1የጭ​ን​ቀት ቀን ሳይ​መጣ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ወራት ፈጣ​ሪ​ህን ዐስብ፤ ደስ አያ​ሰ​ኙም የም​ት​ላ​ቸው ዓመ​ታት ሳይ​ደ​ርሱ፥ 2ፀሓ​ይና ብር​ሃን፥ ጨረ​ቃና ከዋ​ክ​ብ​ትም ሳይ​ጨ​ልሙ፥ ደመ​ና​ትም ከዝ​ናብ በኋላ ሳይ​መ​ለሱ፥ 3ቤት ጠባ​ቆች በሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጡ​በት፥ ኀያ​ላን ሰዎ​ችም በሚ​ጐ​ብ​ጡ​በት፥ ጥቂ​ቶች ሆነ​ዋ​ልና ፈጭ​ታ​ዎች ሥራ በሚ​ፈ​ቱ​በት፥ በመ​ስ​ኮ​ትም ሆነው የሚ​መ​ለ​ከቱ በሚ​ጨ​ል​ሙ​በት፥ 4በአ​ደ​ባ​ባ​ይም ደጆቹ በሚ​ዘ​ጉ​በት ቀን፥ የወ​ፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከዎፍ ድምፅ የተ​ነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚ​ጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፤ 5ከፍ ያለ​ውን ተመ​ል​ክ​ተው ደግሞ ሲፈሩ፥ ድን​ጋ​ጤም በመ​ን​ገድ ላይ ሲሆን፤ ለው​ዝም ሲያ​ብብ፥ አን​በ​ጣም እንደ ሸክም ሲከ​ብድ፥ ፍሬም ሳይ​በ​ተን፤ ሰው ወደ ዘለ​ዓ​ለም ቤቱ ሲሄድ፥ አል​ቃ​ሾ​ችም በአ​ደ​ባ​ባይ ሲዞሩ፤ 6የብር ድሪ ሳይ​በ​ጠስ፥ የወ​ር​ቅም ኵስ​ኵ​ስት ሳይ​ሰ​በር፥ ማድ​ጋ​ውም በም​ንጭ አጠ​ገብ ሳይ​ከ​ሰ​ከስ፥ ወደ መስ​ኮት የሚ​ያዩ ዐይ​ኖች ሳይ​ጠፉ፥ የአ​ደ​ባ​ባይ ደጆች ሳይ​ዘጉ፥ ስለ ቃላት ድን​ጋጤ ከጠ​ላት ቃል የተ​ነሣ የሚ​ጮኹ ሳይ​ነሡ፥ በአ​ዳም ልጆች ሁሉ ወዮታ ሳይ​ሆን፥ ወደ ላይም ሳይ​መ​ለ​ከቱ፥ በመ​ን​ገ​ድም ፍር​ሀት ሳይ​መጣ፥ እሳ​ትም ወደ ላይ ከፍ ማለ​ትን በወ​ደደ ጊዜ ሳይ​ታይ፥ በአ​ደ​ባ​ባይ ልቅሶ ሳይ​ሰማ፥ የብር መልኩ ሳይ​ለ​ወጥ፥ የወ​ር​ቅም መልኩ ሳይ​ጠፋ፥ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሩም በጕ​ድ​ጓድ ላይ ሳይ​ሰ​በር፥ 7አፈ​ርም ወደ ነበ​ረ​በት ምድር ሳይ​መ​ለስ፥ ነፍ​ስም ወደ ሰጠው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​መ​ለስ በሥ​ጋም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይ​ሰጥ ፈጣ​ሪ​ህን አስብ።
8ሰባ​ኪው አለ፥ “ሁሉ ከንቱ፥ የከ​ንቱ ከንቱ ነው።” 9ሰባ​ኪ​ውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕ​ዝቡ ዕው​ቀ​ትን አስ​ተ​ማረ፥ ጆሮ​ውም እን​ቆ​ቅ​ል​ሽን መረ​መረ። 10ሰባ​ኪ​ውም ያማ​ረ​ውን በቅ​ንም የተ​ጻ​ፈ​ውን እው​ነ​ተ​ኛ​ው​ንም ቃል መር​ምሮ ለማ​ግ​ኘት ፈለገ።
11የጠ​ቢ​ባን ቃል እንደ በሬ መው​ጊያ ነው፥ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​ትም ከአ​ንድ እረኛ የተ​ሰ​ጡት ቃላት እንደ ተቸ​ነ​ከሩ ችን​ካ​ሮች ናቸው። 12ከዚ​ህም ሁሉ በላይ፥ ልጄ ሆይ፥ ተግ​ሣ​ጽን ስማ፥ ፍጻሜ የሌ​ላ​ቸው ብዙ መጻ​ሕ​ፍ​ትን አታ​ድ​ርግ። እጅ​ግም ምር​ምር ሰው​ነ​ትን ያደ​ክ​ማል።
13የነ​ገ​ሩን ሁሉ ፍጻሜ ስማ፤ ይህ የሰው ሁለ​ን​ተ​ናው ነውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ጠብቅ። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራን ሁሉ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም ነገር ሁሉ፥ መል​ካ​ምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመ​ጣ​ዋ​ልና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ