የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 4

4
የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ታዛ​ዦች እን​ዲ​ሆኑ የተ​ሰጠ ምክር
1“አሁ​ንም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ጉ​አ​ቸው፥ በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ድ​ት​በ​ዙም፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ገብ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ወ​ርሱ፥ ዛሬ የማ​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ። 2ዛሬ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ እንጂ ባዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ቃል ላይ አት​ጨ​ም​ሩም፤ ከእ​ር​ሱም አታ​ጐ​ድ​ሉም። 3ብዔ​ል​ፌ​ጎ​ርን የተ​ከ​ተ​ለ​ውን ሰው ሁሉ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ለይቶ አጥ​ፍ​ቶ​ታ​ልና አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ዔ​ል​ፌ​ጎር ያደ​ረ​ገ​ውን ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋል። 4እና​ንተ ግን አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የተ​ከ​ተ​ላ​ችሁ እስከ ዛሬ ድረስ ሁላ​ችሁ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ። 5እነሆ፥ እና​ንተ ገብ​ታ​ችሁ በም​ት​ወ​ር​ሱ​አት ምድር ውስጥ እን​ዲህ ታደ​ርጉ ዘንድ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘኝ ሥር​ዐ​ትና ፍር​ድን አሳ​የ​ኋ​ችሁ። 6ጠብ​ቁት፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ ይህን ሥር​ዐት ሁሉ ሰም​ተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢ​ብና አስ​ተ​ዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአ​ሕ​ዛብ ፊት ጥበ​ባ​ች​ሁና ማስ​ተ​ዋ​ላ​ችሁ ይህ ነውና፤ 7አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ን​ጠ​ራው ጊዜ ሁሉ እን​ደ​ሚ​ቀ​ር​በን፥ አም​ላኩ ወደ እርሱ የቀ​ረ​በው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው? 8ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ እን​ደ​ማ​ኖ​ራት እን​ደ​ዚ​ህች ሕግ ሁሉ ጽድቅ የሆ​ነች ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ያለው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?
9“ለራ​ስህ ዕወቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህን ፈጽ​መህ ጠብቅ፤ ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​ትን ይህን ሁሉ ነገር አት​ርሳ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ ከል​ቡ​ናህ አይ​ውጣ፤ ለል​ጆ​ች​ህና ለልጅ ልጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ወደ እኔ ሰብ​ስ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ በም​ድር ላይ በሕ​ይ​ወት በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ እኔን መፍ​ራት ይማ​ሩና ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎ​ኛ​ልና በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ በፈ​ጣ​ሪ​ያ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ቆማ​ችሁ ንገ​ራ​ቸው። 11እና​ን​ተም ቀር​ባ​ችሁ ከተ​ራ​ራው በታች ቆማ​ችሁ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም እስከ ሰማይ ድረስ በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ጨለ​ማና አውሎ ነፋስ፥ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማም ነበረ። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ተና​ገ​ራ​ችሁ፤ የቃ​ልን ድምፅ ሰማ​ችሁ፤ ከድ​ምፅ በቀር መል​ክን ግን አላ​ያ​ች​ሁም። 13ታደ​ር​ጉ​ትም ዘንድ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ቃል ኪዳን ዐሥ​ሩን ቃላት ነገ​ራ​ችሁ፤ በሁ​ለ​ቱም የድ​ን​ጋይ ጽላት ላይ ጻፋ​ቸው። 14ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ተሻ​ግ​ራ​ችሁ በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር የም​ታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ አስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚ​ያን ጊዜ አዘ​ዘኝ።
ከጣ​ዖት አም​ል​ኮት ስለ መራቅ የተ​ሰጠ ማስ​ጠ​ን​ቀ​ቂያ
15“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ተራራ በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ በተ​ና​ገ​ራ​ችሁ ቀን መል​ኩን ከቶ አላ​ያ​ች​ሁ​ምና ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን እጅግ ጠብቁ፤ 16እን​ዳ​ት​በ​ድሉ፥ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል፥ የማ​ና​ቸ​ው​ንም ነገር ምሳሌ፥ በወ​ንድ ወይም በሴት መልክ የተ​ሠ​ራ​ውን፥ በም​ድር ላይ ያለ​ውን፥ 17የእ​ን​ስ​ሳን ሁሉ ምሳሌ ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች የሚ​በ​ር​ረ​ውን የወ​ፍን ሁሉ ምሳሌ፥ 18በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ሽ​ከ​ረ​ከ​ረ​ውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ውስጥ የሚ​ኖ​ረ​ውን የዓ​ሣን ሁሉ ምሳሌ አታ​ድ​ርጉ፤ 19ወደ ሰማይ አት​መ​ል​ከት፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕ​ዛብ ሁሉ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን፥ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንና የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት ሁሉ አይ​ተህ፥ ሰግ​ደ​ህ​ላ​ቸው፥ አም​ል​ከ​ሃ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​ስት ተጠ​ን​ቀቅ። 20እና​ን​ተን ግን እንደ ዛሬው ሁሉ የር​ስቱ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስዶ ከብ​ረት እቶን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ችሁ። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ንተ በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁት ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳ​ል​ሻ​ገር፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ወደ መል​ካ​ሚቱ ምድር እን​ዳ​ል​ገባ ማለ። 22እኔ ግን በዚ​ህች ምድር እሞ​ታ​ለሁ። ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም አል​ሻ​ገ​ርም፤ እና​ንተ ግን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ያች​ንም መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ። 23ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን እን​ዳ​ት​ረሱ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የከ​ለ​ከ​ለ​ውን፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እን​ግ​ዲህ ተጠ​ን​ቀቁ። 24አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​በላ እሳት፥ ቀና​ተ​ኛም አም​ላክ ነውና።
25“ልጆ​ችን፥ የልጅ ልጆ​ች​ንም በወ​ለ​ዳ​ችሁ ጊዜ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ረዥም ዘመን በተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥ በበ​ደ​ላ​ች​ሁም ጊዜ፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ፥ ታስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ የሆ​ነ​ውን ነገር በሠ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ 26ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ከም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ድ​ት​ጠፉ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በእ​ና​ንተ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ፈጽ​ሞም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም። 27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይበ​ት​ና​ች​ኋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በው​ስ​ጣ​ቸው በሚ​ያ​ኖ​ራ​ችሁ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከ​ልም በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሆና​ችሁ ትቀ​ራ​ላ​ችሁ። 28በዚ​ያም የማ​ያ​ዩ​ትን፥ የማ​ይ​ሰ​ሙ​ት​ንም፥ የማ​ይ​በ​ሉ​ት​ንም፥ የማ​ያ​ሸ​ቱ​ት​ንም፥ በሰው እጅ ከእ​ን​ጨ​ትና ከድ​ን​ጋይ የተ​ሠ​ሩ​ትን ሌሎች አማ​ል​ክት ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ። 29ነገር ግን ከዚያ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትሻ​ላ​ችሁ፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ በል​ብ​ህም ሁሉ፥ በነ​ፍ​ስ​ህም ሁሉ​የ​ፈ​ለ​ግ​ኸው እንደ ሆነ ታገ​ኘ​ዋ​ለህ። 30ይህም ሁሉ ነገር በመ​ጨ​ረ​ሻው ዘመን ይደ​ር​ስ​ብ​ሃል፤ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትመ​ለ​ሳ​ለህ፤ ቃሉ​ንም ትሰ​ማ​ለህ። 31አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓሪ አም​ላክ ነውና አይ​ተ​ው​ህም፤ አያ​ጠ​ፋ​ህ​ምም፤ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ቃል ኪዳ​ኑን አይ​ረ​ሳም።
32“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰውን በም​ድር ላይ ከፈ​ጠ​ረው ጀምሮ፥ ከሰ​ማይ ዳር እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ከቶ እን​ዲህ ያለ ታላቅ ነገር ሆኖ፥ ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰ​ምቶ እንደ ሆነ ከአ​ንተ በፊት የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን ጠይቅ። 33አንተ ከእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ሲና​ገር የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ እንደ ሰማ​ህና በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ለህ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ እንደ ሆነ፥ 34አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በግ​ብፅ ለእ​ና​ንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈ​ተ​ናና በተ​አ​ም​ራት፥ በድ​ን​ቅና በሰ​ልፍ፥ በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ማስ​ፈ​ራ​ራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሌላ ሕዝብ መካ​ከል ገብቶ ለእ​ርሱ ሕዝ​ብን ይወ​ስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥ 35እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አም​ላክ እንደ ሆነና ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ እን​ድ​ታ​ውቅ፥ 36ያስ​ተ​ም​ርህ ዘንድ ከሰ​ማይ ድም​ፁን አሰ​ማህ፤ በም​ድ​ርም ላይ ታላ​ቁን እሳት አሳ​የህ፤ ከእ​ሳ​ቱም መካ​ከል ቃሉን ሰማህ። 37አባ​ቶ​ች​ህን ወድ​ዶ​አ​ልና ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ዘራ​ቸ​ውን መረጠ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ሆኖ በታ​ላቅ ኀይሉ ከግ​ብፅ አወ​ጣህ፤ 38ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከግ​ብፅ ከአ​ንተ የጸ​ኑ​ትን ታላ​ላ​ቆ​ቹን አሕ​ዛብ በፊ​ትህ እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ አን​ተ​ንም እን​ዲ​ያ​ገ​ባህ፥ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ርስት አድ​ርጎ እን​ዲ​ሰ​ጥህ፥ 39እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ በሰ​ማይ በታ​ችም በም​ድር አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደ ሌለ ዛሬ ዕወቅ፤ በል​ብ​ህም ያዝ። 40ለእ​ና​ንተ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ይሆን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ ይረ​ዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ጠብቁ።”
ለነ​ፍሰ ገዳ​ዮች የተ​ፈ​ቀዱ ከተ​ሞች
41በዚ​ያን ጊዜ ሙሴ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሦስት ከተ​ሞ​ችን ለየ። 42ትና​ንት፥ ከት​ናት በስ​ቲ​ያም ጠላቱ ያል​ሆ​ነ​ውን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ሳያ​ውቅ የገ​ደለ ገዳዩ ይማ​ፀ​ን​ባ​ቸው ዘንድ፥ ከእ​ነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ተማ​ፅኖ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ፤ 43ለሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳ በደ​ል​ዳላ ስፍራ ያለ ባሶር፥ ለጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ያለ ራሞት፥ ለም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ያለ ጎላን ነበሩ።
ስለ ሕግ​ጋቱ የተ​ሰጠ ማብ​ራ​ሪያ
44ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ያኖ​ራት ሕግ ይህች ናት፤ 45ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ና​ገ​ረው ምስ​ክ​ርና ሥር​ዐት፤ ፍር​ድም ይህ ነው። 46ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ቱት፥ በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ በነ​በ​ረው በአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ በሴ​ዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አቅ​ራ​ቢያ ባለው ሸለቆ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፤ 47የእ​ር​ሱ​ንና የባ​ሳ​ንን ንጉሥ፥ የዐ​ግን ምድር፥ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በ​ሩ​ትን የሁ​ለ​ቱን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ንን ነገ​ሥ​ታት ምድር ወሰዱ። 48በአ​ር​ኖን ወንዝ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ እስከ ሴዎን ተራራ እስከ ኤር​ሞን ድረስ፥ 49በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ መሿ​ለ​ኪያ ካለው ከአ​ሴ​ዶን#ዕብ. “ከፈ​ስጋ” ይላል። ተራራ በታች ያለ​ውን ዓረባ ሁሉ ወሰዱ።#ዕብ. “እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ” የሚል ይጨ​ም​ራል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ