የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 30:1-10

ኦሪት ዘዳ​ግም 30:1-10 አማ2000

“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እኔ በፊ​ትህ ያኖ​ር​ሁት ይህ ነገር ሁሉ፥ በረ​ከ​ቱና መር​ገሙ በወ​ረ​ደ​ብህ ጊዜ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​በ​ት​ንህ በዚያ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል ሆነህ በል​ብህ ዐስ​በው፤ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተመ​ለስ፤ እኔም ዛሬ እን​ደ​ማ​ዝ​ዝህ ሁሉ አን​ተና ልጆ​ችህ በፍ​ጹም ልብና በፍ​ጹም ነፍስ ቃሉን ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀጢ​አ​ት​ህን ይቅር ይል​ሃል ይራ​ራ​ል​ህ​ማል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን ከበ​ተ​ነ​በት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል መልሶ ይሰ​በ​ስ​ብ​ሃል። መበ​ተ​ን​ህም እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢሆን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ ይሰ​በ​ስ​ብ​ሃል፤ ከዚ​ያም ያመ​ጣ​ሃል። አባ​ቶ​ች​ህም ወደ ወረ​ሱ​አት ምድር አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ ትወ​ር​ሳ​ት​ማ​ለህ፤ መል​ካ​ምም ነገር ያደ​ር​ግ​ል​ሃል፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ይልቅ ያበ​ዛ​ሃል። በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖር፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ እን​ድ​ት​ወ​ድድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም ልብ ያጠ​ራ​ዋል። አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን መር​ገም ሁሉ በጠ​ላ​ቶ​ች​ህና በሚ​ጠ​ሉህ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ህም ላይ ያመ​ጣ​ታል። አን​ተም ተመ​ል​ሰህ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ትሰ​ማ​ለህ፤ ዛሬም እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ታደ​ር​ጋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ባ​ቶ​ችህ ደስ እን​ዳ​ለው በመ​ል​ካሙ ነገር ሁሉ እንደ ገና በአ​ንተ ደስ ይለ​ዋ​ልና አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ፥ በሆ​ድ​ህም ፍሬ፥ በእ​ር​ሻ​ህም ፍሬ፥ በከ​ብ​ት​ህም ብዛት እጅግ ይባ​ር​ክ​ሃል። በዚህ የሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ትእ​ዛ​ዙን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱን ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ብት​ሰማ፥ በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብት​መ​ለስ ይባ​ር​ክ​ሃል።