በፊትህ ያስቀመጥሁት ይህ በረከትና መርገም ሁሉ በአንተ ላይ ሲመጣና አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በትኖህ በምትኖርበት አሕዛብ መካከል ሆነህ ወደ ልብህ ተመልሰህ ነገሮቹን በምታስተውልበት ጊዜ፣ እንዲሁም ዛሬ እኔ በማዝዝህ ሁሉ መሠረት አንተና ልጆችህ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ተመልሳችሁ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እርሱን ስትታዘዙ፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ምርኮህን ይመልስልሃል፤ ይራራልሃልም፤ አንተን ከበተነበት አሕዛብ መካከልም እንደ ገና ይሰበስብሃል። ከሰማይ በታች እጅግ ሩቅ ወደ ሆነ ምድር ብትጋዝ እንኳ፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከዚያ ይሰበስብሃል፤ መልሶም ያመጣሃል። የአባቶችህ ወደ ሆነችው ምድር ያመጣሃል፤ አንተም ትወርሳታለህ። ከአባቶችህ ይበልጥ ያበለጽግሃል፤ ያበዛሃልም። አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እንድትወድደው፣ በሕይወትም እንድትኖር፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የአንተንና የዘርህን ልብ ይገርዛል። አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ይህን ርግማን ሁሉ በሚጠሉህና በሚያሳድዱህ ጠላቶችህ ላይ ያደርገዋል። አንተም ተመልሰህ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ትታዘዛለህ፤ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ትጠብቃለህ። ከዚያም አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በእጅህ ሥራ ሁሉና በወገብህ ፍሬ፣ በእንስሳትህ ግልገሎችና በምድርህ ሰብል እጅግ ያበለጽግሃል። በአባቶችህ ደስ እንደ ተሰኘ ሁሉ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) አንተንም በማበልጸግ ደስ ይለዋልና። ይህም የሚሆነው፣ አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ከታዘዝህና በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዐቱን በመጠበቅ፣ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ስትመለስ ነው።
ዘዳግም 30 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘዳግም 30
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘዳግም 30:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos