“እግዚአብሔርም እንዳለኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን። እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ ‘ይህን ተራራ መዞር ይበቃችኋል፤ ተመልሳችሁ ወደ መስዕ ሂዱ።’ ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች ሀገር ታልፋላችሁ፤ እነርሱ ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ። የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው። ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገንዘብ በመለኪያ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ። አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ ይህን ታላቅና የሚያስፈራ ምድረ በዳ እንዴት እንደ ዞርኸው ዕወቅ፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፤ ከተናገርኸው ሁሉ አንዳችም አላሳጣህም።
ኦሪት ዘዳግም 2 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘዳግም 2:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች