መጽ​ሐፈ ባሮክ 2

2
1“አም​ላ​ካ​ችን በእ​ኛና እስ​ራ​ኤ​ልን በገዙ መሳ​ፍ​ን​ቶ​ቻ​ችን ላይ፥ በነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን ላይና በመ​ኳ​ን​ን​ቶ​ቻ​ችን ላይ፥ በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃሉን አጸና። 2በሙሴ ኦሪት እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ አደ​ረ​ገው ከሰ​ማይ በታች ያል​ሆነ ክፉ ነገ​ርን በእኛ ላይ ያመጣ ዘንድ፥ ቃሉን አጸና። 3በዚያ ወራት ሰው የወ​ን​ዶች ልጆ​ቹ​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ቹን ሥጋ በላ። 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ር​ሱን በበ​ተ​ነ​በት በዙ​ሪ​አ​ችን በአሉ አሕ​ዛብ ዘንድ ለው​ር​ደ​ትና ለመ​ከራ ይሆኑ ዘንድ በዙ​ሪ​ያ​ችን በአሉ ነገ​ሥት ሁሉ እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። 5ወራ​ዶች ሆንን፤ የከ​በ​ር​ንም አል​ሆ​ንም፤ ለቃሉ ሳን​ታ​ዘዝ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለ​ና​ልና። 6ጽድቅ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ለእ​ኛና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ግን እንደ ዛሬው ዕለት የፊት ኀፍ​ረት ነው። 7በእኛ ላይ የደ​ረ​ሰ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኛ ላይ ተና​ግሮ ነበ​ርና። 8እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ንም ከክፉ ልባ​ችን መን​ገድ እን​መ​ለስ ዘንድ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አል​ጸ​ለ​ይ​ንም። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ከራ ተጋ፤ በእ​ኛም ላይ አመ​ጣው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኛ ላይ ባዘ​ዘው ሥራው ሁሉ ጻድቅ ነውና። 10በፊ​ታ​ችን በሰ​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ እን​ሄድ ዘንድ ቃሉን አል​ሰ​ማ​ንም።
11“አሁ​ንም በጸ​ናች እጅ፥ በተ​አ​ም​ርና በድ​ንቅ ሥራ፤ በታ​ላቅ ኀይ​ልና በተ​ዘ​ጋ​ጀች ክንድ ሕዝ​ብ​ህን ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣህ፥ ዛሬም እንደ ሆነው ለራ​ስህ ታላቅ ስምን ያደ​ረ​ግህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ! 12በደ​ልን፤ ክፉም አደ​ረ​ግን፤ አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ! በሥ​ር​ዐ​ትህ ሁሉ ላይ የማ​ይ​ገባ ሥራን ሠራን። 13ቍጣ​ህን ከእኛ አብ​ርድ፤ እኛን በዚያ በበ​ተ​ን​ህ​በት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ጥቂት ቀር​ተ​ና​ልና። 14ጌታ ሆይ! ልመ​ና​ች​ን​ንና ጸሎ​ታ​ች​ንን ስማ፤ ስለ ስም​ህም ስትል አድ​ነን፤ በማ​ረ​ኩ​ንም ሰዎች ፊት ሞገ​ስን እና​ገኝ ዘንድ ስጠን፤ 15ምድር ሁሉ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን እንደ ሆንህ ታውቅ ዘንድ፥ ስምህ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይና በወ​ገኑ ላይ ተጠ​ር​ቶ​አ​ልና ። 16አቤቱ ከቤተ መቅ​ደ​ስህ ሁነህ ተመ​ል​ከት፤ አቤቱ ጆሮ​ህን ወደ እኛ አዘ​ን​ብ​ለህ ስማን።
17“ዐይ​ኖ​ች​ህን ገል​ጠህ ተመ​ል​ከት፤ አቤቱ ነፍ​ሳ​ቸው ከሥ​ጋ​ቸው የተ​ለ​የች በመ​ቃ​ብር የሚ​ኖሩ ሙታን የሚ​ያ​ከ​ብ​ሩ​ህና የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑህ አይ​ደ​ሉ​ምና። 18ነገር ግን አዝ​ናና ተጨ​ንቃ የም​ት​ኖር፥ በብዙ መከ​ራም ያዘ​ነች ሰው​ነ​ትና የፈ​ዘዙ ዐይ​ኖች፥ የተ​ራ​በ​ችም ነፍስ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ አቤቱ ለጽ​ድ​ቅ​ህም ይገ​ዛሉ። 19አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን በፊ​ትህ ምሕ​ረ​ትን የለ​መ​ን​ንህ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን ጽድቅ አይ​ደ​ለ​ምና። 20በባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ በነ​ቢ​ያት እጅ እንደ ተና​ገ​ርህ መዓ​ት​ህ​ንና መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን በእኛ ላይ ሰድ​ደ​ሃ​ልና።
21“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትከ​ሻ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ተገዙ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ጠ​ኋት ምድ​ርም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ 22የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰሙ፥ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ባት​ገዙ፥ 23የደ​ስ​ታና የሐ​ሤት ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራና የሴት ሙሽራ ድምፅ ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውጭ ይጠ​ፋል፤ ምድ​ርም ሁሉ ከነ​ዋ​ሪ​ዎች ምድረ በዳ ይሆ​ናል። 24ቃል​ህን አል​ሰ​ማ​ንም፤ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አል​ተ​ገ​ዛ​ንም፤ የን​ጉ​ሦ​ቻ​ችን ዐፅ​ሞ​ችና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዐፅ​ሞች ከቦ​ታ​ቸው እን​ደ​ሚ​ወጡ በባ​ሮ​ችህ ነቢ​ያት እጅ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውም ደረ​ሰ​ብን።
25“እነሆ በቀን ሐሩ​ርና በሌ​ሊት ቍር ጣሏ​ቸው፤ ተማ​ረ​ክን፤#“ተማ​ረ​ክን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በቀ​ጠ​ናና በጦር፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ክፉ ሞትን ሞትን። 26በእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ንና በይ​ሁዳ ወገን ኀጢ​አት ምክ​ን​ያት ስምህ የተ​ጠ​ራ​በ​ትን መቅ​ደስ እንደ ዛሬው ዕለት ጣልህ። 27ነገር ግን አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን! እንደ ቸር​ነ​ትህ ሁሉና እንደ ታላቁ ይቅ​ር​ታህ ሁሉ አደ​ረ​ግ​ህ​ልን፤ 28በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ሕግ​ህን ይጽፍ ዘንድ ባዘ​ዝ​ህ​ባት ዕለት በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ በሙሴ እጅ እን​ዲህ ስትል እንደ ተና​ገ​ርህ፥ 29ቃሌን በእ​ው​ነት ባት​ሰሙ ይህች ብዛ​ታ​ችሁ እና​ን​ተን በበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ወደ ጥቂ​ት​ነት ትመ​ለ​ሳ​ለች።
30“እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​ሙ​ኝም ዐወ​ቅ​ኋ​ቸው፤ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ ናቸ​ውና፤ በተ​ሰ​ደ​ዱ​በ​ትም ሀገር ወደ ፈቃ​ዳ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ። 31እኔም አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። ልብን፥ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ። 32ባስ​ማ​ረ​ክ​ኋ​ቸ​ውም ሀገር ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ኛል፤ ስሜ​ንም ያስ​ባሉ። 33ከደ​ን​ዳና ልባ​ቸ​ውና ከክፉ ሥራ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የበ​ደሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም መን​ገድ ያስ​ባሉ። 34ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ለአ​ብ​ር​ሃም፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅና ለያ​ዕ​ቆ​ብም ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ሀገር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ይገ​ዙ​አ​ታ​ልም፤ እኔም አበ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አያ​ን​ሱም። 35አም​ላ​ካ​ቸው እሆ​ና​ቸው ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳ​ንን እሠ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ሕዝቤ እስ​ራ​ኤ​ልን ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ሀገ​ራ​ቸው አላ​ወ​ጣ​ቸ​ውም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ