ትን​ቢተ አሞጽ 5:1-27

ትን​ቢተ አሞጽ 5:1-27 አማ2000

የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ና​ንተ ላይ ለሙሾ የማ​ነ​ሣ​ውን ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ወደ​ቀች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ነ​ሣም፤ በም​ድ​ርዋ ላይ ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ትም የለም። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “ሺህ ከሚ​ወ​ጡ​ባት ከተማ መቶ ይቀ​ራሉ፤ መቶም ከሚ​ወ​ጡ​ባት ከተማ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዐሥር ይቀ​ራሉ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እኔን ፈልጉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጌል​ገላ ፈጽሞ ትማ​ረ​ካ​ለ​ችና፥ ቤቴ​ልም እን​ዳ​ል​ነ​በ​ረች ትሆ​ና​ለ​ችና ቤቴ​ልን አት​ፈ​ልጉ፤ ወደ ጌል​ገ​ላም አት​ሂዱ፤ ወደ ቤር​ሳ​ቤ​ህም አት​ለፉ።” በዮ​ሴፍ ቤት እሳት እን​ዳ​ት​ቃ​ጠል፥ እን​ዳ​ት​በ​ላ​ቸ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት እሳት የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ላ​ቸው እን​ዳ​ያጡ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈልጉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን በሰ​ማይ ያደ​ር​ጋል፤ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ ይመ​ሠ​ር​ታል። ሁሉን የሚ​ሠ​ራና የሚ​ያ​ቅ​ናና፥ ብር​ሃ​ኑን ወደ መስዕ የሚ​መ​ል​ሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚ​ያ​ጨ​ል​መው፥ የባ​ሕ​ሩ​ንም ውኃ ጠርቶ በም​ድር ፊት የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። በኀ​ያ​ላን ላይ ቅጥ​ቃ​ጤን፥ በአ​ን​ባ​ዎ​ችም ላይ ጕስ​ቍ​ል​ናን ያመ​ጣል። በበሩ የሚ​ገ​ሥ​ጸ​ውን ጠሉ፤ እው​ነ​ት​ንም የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ተጸ​የፉ። ድሃ​ው​ንም ደብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ልና፤ መማ​ለ​ጃ​ንም ከእ​ርሱ ወስ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ ያማሩ ቤቶ​ች​ንም መር​ጣ​ችሁ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ነገር ግን አት​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ ያማሩ የወ​ይን ቦታ​ዎ​ችም ተክ​ላ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ወይ​ንን አት​ጠ​ጡም። ጻድ​ቁን የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጉቦ​ንም የም​ት​ቀ​በሉ፥ በበ​ሩም የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ፍርድ የም​ታ​ጣ​ምሙ እና​ንተ ሆይ! በደ​ላ​ችሁ እን​ዴት እንደ በዛ፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም እን​ዴት እንደ ጸና እኔ ዐው​ቃ​ለ​ሁና። ስለ​ዚህ ዘመኑ ክፉ ነውና በዚያ ዘመን አስ​ተ​ዋይ ዝም ይላል። በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ መል​ካ​ሙን ፈልጉ፤ ክፉ​ው​ንም አይ​ደ​ለም፤ እን​ዲሁ እና​ንተ እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል። ክፉ​ውን ጥሉ፤ መል​ካ​ሙ​ንም ውደዱ፤ በበ​ሩም አደ​ባ​ባይ ፍር​ድን አጽኑ፤ ምና​ል​ባት ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዮ​ሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆ​ናል። ስለ​ዚህ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በየ​አ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆ​ናል፤ በየ​መ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባ​ላል፤ ገበ​ሬ​ዎ​ቹም ወደ ልቅሶ፥ አል​ቃ​ሾ​ቹም ወደ ዋይታ ይጠ​ራሉ። በመ​ካ​ከ​ልህ አል​ፋ​ለ​ሁና በጎ​ዳ​ናው ሁሉ ልቅሶ ይሆ​ናል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀን ለም​ት​ፈ​ልጉ ወዮ​ላ​ችሁ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀን ለምን ትፈ​ል​ጋ​ላ​ችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብር​ሃን አይ​ደ​ለም። ከአ​ን​በሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እን​ዳ​ገ​ኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግ​ድ​ግዳ ላይ እን​ዳ​ስ​ደ​ገ​ፈና እባብ እንደ ነደ​ፈው ሰው ይሆ​ናል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ብር​ሃን ሳይ​ሆን ጨለማ አይ​ደ​ለ​ምን? ፀዳል የሌ​ለ​ውም ድቅ​ድቅ ጨለማ አይ​ደ​ለ​ምን? ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁን ጠል​ች​ዋ​ለሁ፤ አር​ቄ​ው​ማ​ለሁ፤ መዓዛ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አላ​ሸ​ትም። የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ና​ች​ሁን ብታ​ቀ​ር​ቡ​ል​ኝም እንኳ አል​ቀ​በ​ለ​ውም፤ የድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም አል​መ​ለ​ከ​ትም። የዝ​ማ​ሬ​ህ​ንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመ​ሰ​ን​ቆ​ህ​ንም ዜማ አላ​ዳ​ም​ጥም። ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድ​ቅም እን​ደ​ማ​ይ​ደ​ርቅ ፈሳሽ ይፍ​ሰስ። “የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በውኑ በም​ድረ በዳ አርባ ዓመት ሙሉ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አቅ​ር​ባ​ች​ሁ​ል​ኛ​ልን? ለራ​ሳ​ች​ሁም የሠ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ውን ምስ​ሎች፥ የሞ​ሎ​ክን ድን​ኳ​ንና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የሬ​ፋ​ንን ኮከብ አነ​ሣ​ችሁ። ስለ​ዚህ ከደ​ማ​ስቆ ወደ​ዚያ አስ​ማ​ር​ካ​ች​ኋ​ለሁ” ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የተ​ባለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።