የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ አሞጽ 4

4
የእ​ስ​ራ​ኤል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለ​መ​መ​ለስ
1በሰ​ማ​ርያ ተራራ የም​ት​ኖሩ፥ ድሆ​ች​ንም የም​ት​በ​ድሉ፥ ችግ​ረ​ኞ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጌቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም፦ አምጡ እን​ጠጣ የም​ትሉ እና​ንተ የባ​ሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ። 2ጌታ አግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እና​ን​ተን በሰ​ልፍ ዕቃ፥ ቅሬ​ታ​ች​ሁ​ንም በመ​ቃ​ጥን የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት ቀን እነሆ በላ​ያ​ችሁ ይመ​ጣል” ብሎ በቅ​ዱ​ስ​ነቱ ምሎ​አል። 3“ዕራ​ቁ​ታ​ች​ሁን ያወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ትተ​ያ​ያ​ላ​ችሁ፤ በሬ​ማ​ንም ተራራ ትጣ​ላ​ላ​ችሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከስ​ሕ​ተት አለ​መ​ማር
4“ወደ ቤቴል ገብ​ታ​ችሁ ኀጢ​አ​ትን ሠራ​ችሁ፤ በጌ​ል​ገ​ላም ኀጢ​አ​ትን አበ​ዛ​ችሁ፤ በየ​ማ​ለ​ዳ​ውም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ በየ​ሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁን አቀ​ረ​ባ​ችሁ፤ 5ሕጉን በውጭ አነ​በ​ባ​ችሁ፤ የታ​መ​ነም አላ​ች​ሁት፤#ዕብ. “እርሾ ከአ​ለ​በት የም​ስ​ጋ​ና​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ” ይላል። በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም የም​ታ​ቀ​ር​ቡ​ትን አው​ጁና አውሩ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
6“በከ​ተ​ማ​ችሁ ሁሉ ጥር​ስን ማጥ​ረ​ስን፥#ዕብ. “ጥር​ስን ማጥ​ራ​ትን” ይላል። በስ​ፍ​ራ​ች​ሁም ሁሉ እን​ጀ​ራን ማጣ​ትን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ እና​ንተ ግን ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 7መከር ሳይ​ደ​ርስ ገና ከሦ​ስት ወር በፊት ዝና​ብን ከለ​ከ​ል​ኋ​ችሁ፤ በአ​ን​ድም ከተማ ላይ አዘ​ነ​ብሁ፤ በሌ​ላ​ውም ከተማ ላይ እን​ዳ​ይ​ዘ​ንብ አደ​ረ​ግሁ፤ በአ​ንድ ወገን ዘነበ፤ ያል​ዘ​ነ​በ​በ​ትም ወገን ደረቀ። 8የሁ​ለት ወይም የሦ​ስት ከተ​ሞች ሰዎች ወደ አን​ዲት ከተማ ውኃ ይጠጡ ዘንድ ሄዱ፤ ነገር ግን አል​ረ​ኩም፤ እና​ንተ ግን ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 9በአ​ባ​ርና በቸ​ነ​ፈር መታ​ኋ​ችሁ፤ አት​ክ​ል​ታ​ችሁ፥ ወይ​ና​ች​ሁና በለ​ሳ​ችሁ፥ ወይ​ራ​ች​ሁም ከበጀ በኋላ ተምች በላው፤ ይህም ሆኖ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 10“በግ​ብፅ እንደ ሆነው ሞትን ሰደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ይፍ ገደ​ልሁ፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ማ​ረ​ክሁ፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁም እሳ​ትን ሰድጄ አጠ​ፋ​ኋ​ችሁ፤ በዚ​ህም ሁሉ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 11ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን አስ​ቀ​ድሜ እንደ ገለ​በ​ጥ​ኋ​ቸው፥ እን​ዲሁ ገለ​በ​ጥ​ኋ​ችሁ፤ እና​ን​ተም ከእ​ሳት ውስጥ እንደ ተነ​ጠቀ ትን​ታግ ሆና​ችሁ፤ በዚ​ህም ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
12“ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል ሆይ! እን​ደ​ዚህ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ! እን​ደ​ዚህ ስለ​ማ​ደ​ር​ግ​ብህ የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም ለመ​ጥ​ራት ተዘ​ጋጅ። 13እነሆ ነጐ​ድ​ጓ​ድን የሚ​ያ​ጸና፥ ነፋ​ስ​ንም የፈ​ጠረ፥ የመ​ሢ​ሕን ነገር#ዕብ. “የል​ቡን አሳብ” ይላል። ለሰው የሚ​ነ​ግር፥ ንጋ​ትን ጭጋግ የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ከፍ​ታ​ዎች ላይ የሚ​ረ​ግጥ፥ ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ